የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 8/07 ገጽ 15
  • “የዘላለማዊቷ ከተማ” ድምፅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የዘላለማዊቷ ከተማ” ድምፅ
  • ንቁ!—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሰዎች ለምን ያህል ዓመት መኖር ይችላሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
ንቁ!—2007
g 8/07 ገጽ 15

“የዘላለማዊቷ ከተማ” ድምፅ

ጣሊያን የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

ኦቶሪኖ ሬስፒጊ የተባለ ጣሊያናዊ የሙዚቃ አቀናባሪ በሮም የሚገኙ በርካታ ፏፏቴዎችን ከተመለከተና ድምፃቸውን ከሰማ በኋላ “የሮም ፏፏቴዎች” የሚል ርዕስ ያለው ሙዚቃ አቀናብሯል። ከእነዚህ መካከል በውበቱ ተወዳዳሪ የሌለውን ትሬቪ የተባለውን ፏፏቴ እንመልከት።

ወደ ፏፏቴው የሚያመራውን ቀጭን መንገድ ይዘን ከሄድን በኋላ እጥፍ እንዳልን የሚታየው ነገር በጣም አስደናቂ ነው። ሃያ ሜትር ስፋትና ከቤተ መንግሥቱ ጫፍ አንስቶ እስከ ውኃው ሥር ድረስ 26 ሜትር ከፍታ ያለው ትልቁ የትሬቪ ፏፏቴ አነስተኛ መጠን ባለው አደባባይ ላይ ጎልቶ ይታያል። በዚህ ጠባብ ቦታ ላይ የሚገኘው ይህ ፏፏቴ ምንኛ የሚያስደንቅ ነው!

ትሬቪ ተብሎ የሚጠራው ይህ ፏፏቴ እንዲሠራ ያዘዙት ሊቀ ጳጳስ ክሌመንት አሥራ ሁለተኛ ሲሆኑ ንድፉን ያወጣው ደግሞ ጣሊያናዊው ኒኮሎ ሳልቪ ነው። ግንባታው በ1732 ተጀምሮ በ1762 ተጠናቀቀ። ፏፏቴው ውኃ የሚያገኘው በመጀመሪያው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት በተገነባውና ከከተማዋ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አኩዋ ቪርጎ በተባለ ቦይ አማካኝነት ነው።

ከቤተ መንግሥቱ ሕንጻ ጋር ተያይዞ የተሠራው ይህ ፏፏቴ የተነደፈው ሰዎች ልክ ባሕር ዳር እንዳሉ ሆኖ እንዲሰማቸው ታስቦ ነው። በአፈ ታሪክ የሚነገርለት ኦሲየነስ (አንዳንዶች ኔፕቱን ይሉታል) የተባለው የባሕር አምላክ የተለየ ቅርጽ ባለው ሰረገላ ላይ በኩራት ተቀምጦ ከሥሩ የሚፈሰውን የፏፏቴ ውኃ የሚቆጣጠር ይመስላል። ውኃው በሌሎቹ ሐውልቶች አጠገብ አልፎ ከታች በሚገኙት አለቶች ላይ ኮለል እያለ ሲወርድ የሚፈጥረው ድምፅ የባሕር ሞገድ ከባሕር ዳርቻ ጋር ሲጋጭ የሚያሰማውን ድምፅ ይመስላል። ውኃው የተጠራቀመበት ቦታ የአደባባዩን አብዛኛውን ክፍል ሸፍኖታል። ይህ ደግሞ መላውን አደባባይ የፏፏቴው ክፍል አስመስሎታል።

በየዕለቱ ወደዚህ አነስተኛ አደባባይ የሚጎርፉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች የሮም ትልቁ የቱሪስት መስህብ በሆነው በዚህ ፏፏቴ ውስጥ ሳንቲም ይጥላሉ። በሳምንት አንድ ቀን ከታች የተጠራቀመው ውኃ እንዲፈስ ከተደረገ በኋላ ጎብኚዎቹ የጣሉት ሳንቲም ይሰበሰባል፤ ይህ በአማካይ ወደ 11,000 የአሜሪካ ዶላር የሚያህል ገንዘብ ሃይማኖታዊ ለሆነ አንድ በጎ አድራጎት ድርጅት ይሰጣል።

ሬስፒጊ እንዳለው የሮም ጎብኚዎች ያደነቋቸው በከተማዋ ውስጥ የሚገኙት ፏፏቴዎች እንደ አንድ የሙዚቃ ቡድን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚዘምሩ ከሆነ ጎላ ብሎ የሚሰማው ድምፅ የትሬቪ ፏፏቴ ይሆናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ