ቤተሰብ የሚወያይበት
በዚህ ሥዕል ላይ ምን ስህተቶች ይታዩሃል?
ዮሐንስ 6:5-13ን አንብብ። በዚህ ሥዕል ላይ ስህተት የሆኑት ሦስት ነገሮች የትኞቹ ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ፤ እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።
1 ․․․․․
2 ․․․․․
3 ․․․․․
ውይይት፦
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ምን እንዲሰበስቡ ነገራቸው? ለምን? ይህስ ስለ ኢየሱስ ምን ያስተምርሃል? አንተስ አባካኝ እንዳትሆን ምን ማድረግ ትችላለህ?
ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦
ዮሐንስ 6:5-13ን በጋራ አንብቡ። የሚቻል ከሆነ አንደኛው ሰው ተራኪውን፣ ሁለተኛው ሰው ኢየሱስን፣ ሦስተኛው ሰው ፊልጶስን እና አራተኛው ሰው ደግሞ እንድሪያስን ወክሎ እንዲያነብ አድርጉ።
ካርድ በመሰብሰብ መማር
ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው
የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 1 ኢያሱ
ጥያቄ
ሀ. ኢያሱና ሠራዊቱ የኢያሪኮን ቅጥር ማፍረስ የቻሉት እንዴት ነው?
ለ. ኢያሱ የተናገረውን ዓረፍተ ነገር ሙላ፦ ‘እኔና ቤቴ ግን . . .’
ሐ. ኢያሱ የሚጠራባቸው ሌሎች ስሞች የትኞቹ ናቸው?
[ሠንጠረዥ]
4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ
ኢያሱ የኖረበት ዘመን 1500ዎቹ ዓ.ዓ. ገደማ
1 ዓ.ም.
98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ
[ካርታ]
ከግብፅ ወደ ተስፋይቱ ምድር ተጉዟል
ግብፅ
ተስፋይቱ ምድር
ኢያሱ
አጭር የሕይወት ታሪክ፦
የነዌ ልጅ ነበር። የሙሴ አገልጋይ የነበረ ሲሆን ከጊዜ በኋላ እስራኤላውያንን እንዲመራ ተሹሟል። (ዘፀአት 33:11፤ ዘዳግም 34:9፤ ኢያሱ 1:1, 2) ደፋር የነበረው ኢያሱ የአምላክን ሕዝቦች ወደ ተስፋይቱ ምድር መርቷቸዋል። ይሖዋ በሰጣቸው ተስፋዎች ላይ እምነት የነበረው ከመሆኑም ሌላ መመሪያዎቹን ታዟል እንዲሁም እሱን በታማኝነት አገልግሏል።
መልስ
ሀ. አምላክን ታዘው ከተማዋን በመዞራቸው ነው።—ኢያሱ 6:1-27
ለ. ‘. . . ይሖዋን እናገለግላለን።’ —ኢያሱ 24:15
ሐ. ሆሺአ እና የሆሹዋ። —ዘኍልቍ 13:8, 16 NW
ሕዝቦችና አገሮች
4. ቪክቶር እባላለሁ። የ7 ዓመት ልጅ ስሆን የምኖረው በአፍሪካ አህጉር በምትገኘው በማላዊ ነው። በማላዊ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 750, 7,500 ወይስ 75,000?
5. የምኖርበትን አገር በሚጠቁመው ፊደል ላይ አክብብ። አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከማላዊ ምን ያህል የሚርቅ ይመስልሃል?
ሀ
ለ
ሐ
መ
ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።
● በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ ገጽ 22 ላይ ይገኛል
በገጽ 30 እና 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
1. ምግቡን መያዝ ያለበት ወንድ ልጅ እንጂ ሴት ልጅ አይደለችም።
2. ወደ ኢየሱስ ያመጡት አምስት ፖም ሳይሆን አምስት ዳቦ ነበር።
3. ወደ ኢየሱስ ያመጡት ሁለት በቆሎ ሳይሆን ሁለት ዓሣዎችን ነበር።
4. 75,000።
5. ሐ።