የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 1/11 ገጽ 14
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2011
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጀርሞች አነሱ?
  • የሥራ ባሕል መጥፋት
  • የድንበር ውዝግብ “እልባት አገኘ”
  • በሀብታሞችና በድሆች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ ሄዷል
    ንቁ!—2000
  • ተላላፊ በሽታዎች አደገኛ ቢሆኑም መከላከል ይቻላል
    ንቁ!—2001
  • ሥራ ለማግኘት የሚረዱ አምስት ቁልፍ ሐሳቦች
    ንቁ!—2005
  • በ20ኛው መቶ ዘመን የተከሰተ ወረርሽኝ
    ንቁ!—1998
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 1/11 ገጽ 14

ከዓለም አካባቢ

በታንዛኒያ አንድ ዶክተር በአማካይ 64,000 ሰዎችን ያክማል።—ዘ ሲትዝን፣ ታንዛኒያ

‘ቢያንስ 1 ቢሊዮን የሚያህሉ በድህነት የሚኖሩ ሰዎች ሥር በሰደደ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ይሠቃያሉ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚሊኒየሙ የልማት ግብ በ2015 በዓለም ላይ የተራቡ ሰዎችን ቁጥር በከፍተኛ መጠን መቀነስ ቢሆንም እዚህ ግብ ላይ መድረስ የሚቻል አይመስልም።’—ሳይንስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

“በዓለም ላይ ያሉት ታላላቅ የሆኑ 100 የጦር መሣሪያ አምራች ኩባንያዎች” በ2008 የ385 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ትርፍ እንዳገኙ የገለጹ ሲሆን ይህም በ2007 ካገኙት ትርፍ በ39 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይበልጣል።—ስቶክሆልም ኢንተርናሽናል ሪሰርች ኢንስቲትዩት፣ ስዊድን

ጀርሞች አነሱ?

በኢሊኖይ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የኖርዝዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ቶማስ ማክዴድ እንዲህ ብለዋል፦ “አንድ ሰው በሕፃንነቱ እጅግ ንጹሕ በሆነ አካባቢ መኖሩ ትልቅ ሰው በሚሆንበት ጊዜ ሰውነቱ በቀላሉ የሚቆጣ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን ይህ ደግሞ ለተለያዩ በሽታዎች እንደሚያጋልጥ ያደረግነው ጥናት ይጠቁማል።” የፊሊፒንስ ሕፃናትን ከአሜሪካውያን ሕፃናት ጋር በማወዳደር በተደረገ አንድ ጥናት መሠረት በጥቅሉ ሲታይ የፊሊፒንስ ተወላጅ የሆኑት ሕፃናት በልጅነታቸው ከአሜሪካውያኑ የበለጠ በባክቴሪያ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎች ይዘዋቸው ነበር። ይሁን እንጂ ከሚጠበቀው በተቃራኒ አዋቂ በሆኑ ፊሊፒናውያን ደም ውስጥ ሰውነት በሽታን ለመቋቋም የሚያመርተው ፕሮቲን መጠን በጣም ትንሽ ሆኖ ተገኝቷል። ታዲያ ምን መደምደሚያ ላይ መድረስ እንችላለን? አንድ ሰው ብዙ ጊዜ ለሚያጋጥሙ ባክቴሪያዎች በልጅነቱ መጋለጡ ትልቅ ሰው በሚሆንበት ጊዜ ገዳይ በሆኑ በሽታዎች እንዳይጠቃ ሊረዳው ይችላል።

የሥራ ባሕል መጥፋት

በርካታ የፊንላንድ አሠሪዎች፣ አዲሱ ትውልድ ሥራ ላይ ለመቆየት የሚያስፈልጉትን ማኅበራዊ እሴቶች ብዙም የማያውቅ መሆኑ ግራ አጋብቷቸዋል። አን ሚኮላ የተባሉ የምግብ ቤት ሥራ አስኪያጅ ከፊንላንድ ብሔራዊ የዜና ማሰራጫ ኩባንያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዲህ ብለዋል፦ “ተቀጣሪዎቹ የሥራ ሰዓትን የግድ ማክበር እንዳለባቸው አይሰማቸውም፤ እንዲሁም በፈለጉበት ሰዓት መግባትና መውጣት የሚችሉ ይመስላቸዋል።” በምግባራቸውና በአለባበሳቸው ረገድም ቢሆን ችግሮች ታይተዋል። አሠሪዎች በተለይ ከሕዝብ ጋር የሚያገናኝ ሥራ ለሚያከናውኑ ተቀጣሪዎቻቸው ተገቢ የሆነውንና ያልሆነው አለባበስ ለማሳየት ተገድደዋል። በተጨማሪም ጓደኞቻቸው፣ ‘እንዲሁ ሰላም ለማለት’ ሲሉ ብቻ ወደ ሥራ ቦታ የሚመጡ መሆኑ ተቀጣሪዎች በሥራና በግል ሕይወት መካከል ያለው ድንበር እየጠፋባቸው መሆኑን ያሳያል።

የድንበር ውዝግብ “እልባት አገኘ”

በቤንጋል የባሕር ወሽመጥ ከምትገኝ አነስተኛ ደሴት ጋር በተያያዘ በባንግላዴሽና በሕንድ መካከል የነበረው ለረጅም ጊዜ የዘለቀ የይገባኛል ውዝግብ ባሕሩ ከፍ በማለቱ ምክንያት እልባት አግኝቷል። ሕንዳውያን፣ ኒው ሙር የሚሏትና ባንግላዴሾቹ ደግሞ ሳውዝ ታልፓቲ የሚሏት ይህች ሰው የማይኖርባት ደሴት ከባሕር ጠለል በላይ ከ1.9 ሜትር ያለፈ ከፍታ ኖሯት አያውቅም። ይሁን እንጂ በቅርቡ የተነሳ የሳተላይት ፎቶ እንደሚያሳየው ባሕሩ ደሴቷን ሙሉ በሙሉ ሸፍኗታል። የካልካታ ጃዳቭፑር የኦሽኖግራፊክ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሹጋታ ሃዝራ “እነዚህ ሁለት አገሮች ለዓመታት ተወያይተው እልባት ሊያገኙለት ያልቻሉት ውዝግብ በምድር ሙቀት መጨመር ምክንያት ሊፈታ ችሏል” ብለዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ