የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 1/12 ገጽ 27-31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2012
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በዚህ ሥዕል ላይ ምን ስህተቶች ይታዩሃል?
  • ካርድ በመሰብሰብ መማር
  • ሕዝቦችና አገሮች
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 1/12 ገጽ 27-31

ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ሥዕል ላይ ምን ስህተቶች ይታዩሃል?

ዘፍጥረት 24:1-4, 10-23⁠ን አንብብ። በዚህ ሥዕል ላይ ስህተት የሆኑት ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

ለውይይት፦

ርብቃ ምን ጥሩ ባሕርያትን አሳይታለች?

ፍንጭ፦ ምሳሌ 31:17, 27, 29-31⁠ን እና 1 ጴጥሮስ 4:9⁠ን አንብብ።

የርብቃን ምሳሌ መከተል የምትችለው እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ ምሳሌ 11:25⁠ን እና ሮም 12:11⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

ልትረዳው የምትፈልገውን የአንድ ሰው ስም ጻፍ። በመቀጠልም ይህን ሰው ለመርዳት ምን ምን ነገሮችን ማድረግ እንደምትችል በወረቀት ላይ አስፍር፤ ከዚያም የጻፍከውን ለቤተሰቦችህ አሳያቸው። እንዲሁም ለግለሰቡ ምን ልታደርግለት እንደምትችልና መቼ ማድረግ እንዳለብህ ከቤተሰብህ ጋር አብራችሁ ወስኑ። ግለሰቡን ከረዳኸው በኋላ ይህን በማድረግህ ምን እንደተሰማህ ለቤተሰቦችህ ንገራቸው።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 13 ኢዮብ

ጥያቄ

ሀ. ኢዮብ በአጠቃላይ ․․․․․ ወንዶችና ․․․․․ ሴቶች ልጆች ነበሩት።

ለ. ሰይጣን፣ ኢዮብ ምን ነገሮችን እንዲያጣ አደረገ?

ሐ. ኢዮብ የተናገረውን ይህን ዓረፍተ ነገር አሟላ፦ “እስክሞት ድረስ . . .”

[ሠንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

1600 ዓ.ዓ. ገደማ ኢዮብ የኖረበት ዘመን

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

በዖፅ ኖሯል

ተስፋይቱ ምድር

ግብፅ

ዖፅ?

ኢዮብ

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

በአምላክ ፊት ‘ነቀፋ የሌለበትና ቅን’ ሰው ነበር። (ኢዮብ 1:8) ምንም እንኳ ሚስቱና ሌሎች ሰዎች ተጽዕኖ ቢያሳድሩበትም ኢዮብ አምላክን ከማገልገል ወደኋላ ብሎ አያውቅም። (ኢዮብ 1:20-22፤ 2:9, 10) ጽናቱና በዚህ ምክንያት ያገኘው በረከት የሚደርሱብንን መከራዎች በታማኝነት እንድንወጣ ድፍረት ይሰጡናል።​—ኢዮብ 42:12-17፤ ያዕቆብ 5:11

መልስ

ሀ. 14, 6​—ኢዮብ 1:2፤ 42:13

ለ. ከብቶቹን፣ አገልጋዮቹን፣ ልጆቹንና ጤንነቱን​—ኢዮብ 1:13-19፤ 2:4-7

ሐ. “. . . ንጹሕ አቋሜን ከእኔ አላርቅም!”​—ኢዮብ 27:5 NW

ሕዝቦችና አገሮች

4. ስሜ ሉካስ ይባላል። ዕድሜዬ ሰባት ዓመት ሲሆን የምኖረው በጀርመን ነው። በጀርመን ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 60,000፣ 100,000 ወይስ 160,000?

5. የምኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከጀርመን በጣም ይርቃል?

ሀ

ለ

ሐ

መ

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

“ቤተሰብ የሚወያይበት” የሚለውን ዓምድ ተጨማሪ ቅጂ ለማግኘት www.jw.org ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማተም ይቻላል።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 27 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. ግመሎቹ 10 እንጂ 11 መሆን የለባቸውም።

2. ርብቃ ውኃ የሞላችው ገንዳ ውስጥ እንጂ በርሜሎች ውስጥ አይደለም።

3. አገልጋዩ ለርብቃ የሰጣት ቀለበት እና ሁለት አምባሮች እንጂ የአንገት ሐብል አይደለም።

4. 160,000

5. ሐ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ