የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g16 ቁጥር 1 ገጽ 12-13
  • ሊክቴንስታይንን እንጎብኝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሊክቴንስታይንን እንጎብኝ
  • ንቁ!—2016
ንቁ!—2016
g16 ቁጥር 1 ገጽ 12-13
ሊክቴንስታይን ውስጥ የሚገኝ የተሸፈነ ድልድይ

አገሮችና ሕዝቦች

ሊክቴንስታይንን እንጎብኝ

ስዊዘርላንድና ኦስትሪያ የሚያዋስኗትን ሊክቴንስታይንን የሚያሳይ ካርታ

ሊክቴንስታይን በዓለማችን ካሉ ትናንሽ አገሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን በስዊዘርላንድና በኦስትሪያ መካከል በአልፕስ ተራሮች ላይ ትገኛለች። ባለፉት ዘመናት በዚህ አካባቢ ኬልቶች፣ ሪሸናውያን፣ ሮማውያንና አለማኒዎች ኖረዋል። በአሁኑ ጊዜ ካሉት የሊክቴንስታይን ነዋሪዎች መካከል ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት ከ1,500 ዓመታት በፊት በዚህ ቦታ ላይ ይኖሩ የነበሩ የአለማኒ ጎሳ ተወላጆች ናቸው።

የሊክቴንስታይን የሥራ ቋንቋ ጀርመንኛ ቢሆንም ቋንቋውን የሚነገርበት መንገድ ከመንደር መንደር ይለያያል። የሊክቴንስታይን ነዋሪዎች ከሚወዷቸው ምግቦች መካከል ከበቆሎ የሚዘጋጀው ትዩርካሬብል እና አስክኖፍል (ፓስታ በቺዝ) ይገኙበታል።

ሁለት የሊክቴንስታይን ተወዳጅ ምግቦች

አስክኖፍል

በሊክቴንስታይን የሚኖሩ አንዲት ሴትና አንዲት ልጅ በቀለማት ያሸበረቀ የባሕል ልብስ ለብሰው

በቀለማት ያሸበረቀ የባሕል ልብስ

አገሪቷን የሚጎበኙ ቱሪስቶች በበረዶ በተሸፈኑ ተራራዎች፣ አረንጓዴ በሆኑ ሸለቆዎች፣ በወይን እርሻዎችና በመስክ ላይ በሚታዩ የተለያዩ ዕፀዋት ዓይናቸው መማረኩ አይቀሬ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ተራራ ላይ በምትገኘው በዚህች ትንሽ አገር 50 ዓይነት ኦርኪዶችን መስኩ ላይ ማየት እንችላለን። በተጨማሪም በሊክቴንስታይን ቤተ መዘክሮች፣ ቲያትር ቤቶችና የወይን መጥመቂያዎች ይገኛሉ። በመሆኑም በበጋም ሆነ በክረምት ቱሪስቶች ሊጎበኟት ይመጣሉ።

የይሖዋ ምሥክሮች ከ1920ዎቹ ጀምሮ በሊክቴንስታይን ሲሰብኩ ቆይተዋል። በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ 90 ገደማ የሚሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች አሉ፤ እነሱም የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ለከተማዋ ነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ያስተምራሉ።

በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀው ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ የሊክቴንስታይን የሥራ ቋንቋ በሆነው በጀርመንኛ ታትሟል፤ መጽሐፉ www.jw.org ላይም ይገኛል።

አጭር መረጃ

  • የሕዝብ ብዛት፦ 37,000

  • ዋና ከተማ፦ ቫዱዝ

  • የሥራ ቋንቋ፦ ጀርመንኛ

  • ሃይማኖት፦ በዋነኝነት የሮም ካቶሊክ

እውቀትህን ፈትሽ

ሊክቴንስታይንን በትክክል የሚገልጻት የትኛው ነው?

  1. ሀ. በዓለም ላይ የባሕር በር በሌላቸው አገሮች ከተከበቡ ሁለት አገሮች አንዷ ናት።

  2. ለ. ከ50 በላይ የተለያዩ የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎች በዚያ ይገኛሉ።

  3. ሐ. በአገሪቱ 1,600 ገደማ የሚሆኑ የተለያዩ የአትክልት ዝርያዎች ይገኛሉ።

  4. መ. የጦር ሠራዊት የሌላት አገር ናት።

መልስ፦ አራቱም ዓረፍተ ነገሮች እውነት ናቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ