የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g17 ቁጥር 6 ገጽ 3
  • ዓለማችን ምንም ተስፋ የለውም?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዓለማችን ምንም ተስፋ የለውም?
  • ንቁ!—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሳይንቲስቶች የመዓት ቀን ሰዓት እንዲጠጋ ወሰኑ—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2012
  • የዓለም መጨረሻ—ቀልብ የሚስብ ርዕስ
    ንቁ!—2012
  • የዓለም ፍጻሜ ቀርቧል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2017
g17 ቁጥር 6 ገጽ 3
የጥፋት ቀን ሰዓት

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | ዓለማችን ምንም ተስፋ የለውም?

ዓለማችን ምንም ተስፋ የለውም?

ሳይንቲስቶች በ2017 መጀመሪያ ላይ አንድ አስደንጋጭ መግለጫ አውጥተው ነበር። በጥር ወር አንድ የሳይንቲስቶች ቡድን ዓለማችን ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ጥፋት ወደሚከሰትበት ጊዜ ይበልጥ እንደቀረበ አስታወቀ። ሳይንቲስቶቹ ዓለም አቀፍ ጥፋት ወደሚከሰትበት ጊዜ ምን ያህል እንደቀረብን የሚያሳየውን ምሳሌያዊ የጥፋት ቀን ሰዓት 30 ሴኮንድ ወደፊት እንዲሄድ አድርገውታል። በአሁኑ ጊዜ ይህ ሰዓት እኩለ ሌሊት ሊል የቀረው ሁለት ደቂቃ ተኩል ብቻ ነው፤ ዓለማችን ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ ከነበረው ሁኔታ አንጻር ሲታይ ለዓለም አቀፍ ጥፋት ይህን ያህል የተቃረበበት ጊዜ የለም!

ሳይንቲስቶች ዓለማችን በተለምዶ የዓለም መጨረሻ ተብሎ ለሚጠራው ጊዜ ምን ያህል እንደተቃረበ ለማወቅ በ2018 ድጋሚ ግምገማ ለማካሄድ እቅድ ይዘዋል። የጥፋትን ቀን የሚያመለክተው ሰዓት አሁንም ከዚህ በፊት ተከስቶ የማያውቅ ታላቅ ጥፋት መከሰቱ እንደማይቀር ይጠቁም ይሆን? አንተ ምን ይመስልሃል? ዓለማችን ምንም ተስፋ የለውም? ምናልባት ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ መስጠት ይከብድህ ይሆናል። በመስኩ ጥናት የሚያደርጉ ባለሙያዎችም እንኳ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። በዓለማችን ላይ ጥፋት መከሰቱ አይቀርም ብለው የሚያምኑት ሁሉም አይደሉም።

እንዲያውም ወደፊት ብሩህ ጊዜ እንደሚመጣ የሚያምኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች የሰው ዘር ተጠራርጎ እንደማይጠፋና ፕላኔታችን ለዘላለም እንደምትኖር እንዲሁም የኑሮ ሁኔታችን እንደሚሻሻል የሚጠቁም ማስረጃ እንዳላቸው ይናገራሉ። የሚያቀርቡት ማስረጃ አሳማኝ ነው? በእርግጥ ዓለማችን ተስፋ አለው ወይስ የለውም?

“የጥፋት ቀን ሰዓት የገዛ ራሳችንን ሥልጣኔ እኛው ራሳችን በሠራናቸው አደገኛ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለማጥፋት ምን ያህል እንደተቃረብን የሚያሳይ ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠው ንድፍ ነው። አንደኛውና ዋነኛው የጥፋት ምክንያት የኑክሌር የጦር መሣሪያ ነው፤ በአየር ንብረት ላይ ለውጥ የሚያስከትሉ ቴክኖሎጂዎች፣ እንደ አዲስ ብቅ ማለት የጀመሩ ባዮቴክኖሎጂዎችና የኢንተርኔት ቴክኖሎጂም ከጥፋቱ መንስኤዎች መካከል ይካተታሉ፤ እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሆን ተብሎም ሆነ በስህተት ወይም በአደጋ፣ በምድራችንና በአኗኗራችን ላይ ሊሻር የማይችል ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ።”—ቡለቲን ኦቭ ዚ አቶሚክ ሳይንቲስትስ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ