ጥንታዊ ሆኖም ዘመናዊ መጽሐፍ
ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል እንደሆነ ያምናሉ። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ሃይማኖታዊ መመሪያዎችን ብቻ የያዘ መጽሐፍ አይደለም። ለዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚሆን ጠቃሚ ምክርም ይዟል።
ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በማንበባቸውና ምክሩን በሥራ ላይ በማዋላቸው ጥቅም አግኝተዋል፤ አንዳንዶቹ የሰጡትን ሐሳብ እንመልከት፦
“ሕይወቴ ይበልጥ የተረጋጋ ሆኗል። አእምሯዊና ስሜታዊ ጤንነቴ ተሻሽሏል። ይበልጥ አዎንታዊ ሆኛለሁ።”—ፊዮና
“መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናቴ የሕይወትን ዓላማና ትርጉም መረዳት ችያለሁ።”—ግኒትኮ
“ሕይወቴ በእጅጉ ተሻሽሏል። በሥራ ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ ለቤተሰቤ ተጨማሪ ጊዜ መስጠት ጀምሬያለሁ።”—አንድሩ
እንዲህ የሚሰማቸው ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ብቻ አይደሉም። በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ለዕለት ተዕለት ሕይወት የሚጠቅሙ ብዙ መመሪያዎችን እንደያዘ ተገንዝበዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ በሚከተሉት የሕይወታችን ዘርፎች የሚጠቅመን እንዴት እንደሆነ እንመልከት፦
አካላዊ ጤንነት
ስሜታዊ ጤንነት
የቤተሰብ ሕይወትና ጓደኝነት
የገንዘብ አያያዝ
መንፈሳዊነት
ቀጣዮቹ ርዕሶች መጽሐፍ ቅዱስ ሃይማኖታዊ መመሪያዎችን ከመስጠት ባለፈ ተጨባጭ በሆነ መንገድ የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ያብራራሉ።