የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 1 ገጽ 4
  • የውጥረት መንስኤ ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የውጥረት መንስኤ ምንድን ነው?
  • ንቁ!—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ውጥረት—መንስኤዎቹና የሚያስከትላቸው ችግሮች
    ንቁ!—2005
  • ጥሩና መጥፎ ውጥረት
    ንቁ!—1998
  • ውጥረትን መቆጣጠር የምንችልበት መንገድ
    ንቁ!—2010
  • በትምህርት ቤት የሚያጋጥመኝን ውጥረት እንዴት ልቋቋመው?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 1 ገጽ 4

ከውጥረት እፎይታ ማግኘት

የውጥረት መንስኤ ምንድን ነው?

ማዮ ክሊኒክ እንደገለጸው “አብዛኞቹ ሰዎች በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንዳሉ ይናገራሉ። ሕይወት በአሁኑ ጊዜ በለውጦችና ባልተጠበቁ ሁኔታዎች የተሞላ ነው።” ውጥረት ከሚያስከትሉ ለውጦችና ያልተጠበቁ ሁኔታዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

  • ፍቺ

  • የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት

  • ከባድ ሕመም

  • ድንገተኛ አደጋ

  • ወንጀል

  • በሩጫ የተሞላ ሕይወት

  • ሰው ሠራሽ ወይም የተፈጥሮ አደጋዎች

  • በትምህርት ቤት ወይም በሥራ ቦታ የሚያጋጥም ጫና

  • ከሥራና ከመተዳደሪያ ጋር የተያያዘ ጭንቀት

ከሥራ መባረር

የአሜሪካ የሥነ ልቦና ማኅበር እንዲህ ብሏል፦ “ከሥራ መባረር ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፤ ግለሰቡ ሊታመም፣ በትዳሩ ውስጥ ችግር ሊያጋጥመው፣ በመንፈስ ጭንቀት ሊዋጥ አልፎ ተርፎም ራሱን ሊያጠፋ ይችላል። ከሥራ መባረር ሁሉንም የሕይወት ዘርፎች ይነካል።”

በልጅነት የሚያጋጥም ውጥረት

ልጆችም ውጥረት ሊያጋጥማቸው ይችላል። አንዳንዶች በትምህርት ቤት ጉልበተኞች ያስቸግሯቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ ቤት ውስጥ ችላ ይባላሉ። አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም ፆታዊ ጥቃት የሚሰነዘርባቸው ልጆችም አሉ። ብዙ ልጆች የትምህርት ውጤትና የፈተና ጉዳይ ያስጨንቃቸዋል። አንዳንድ ልጆች ደግሞ ወላጆቻቸው በመፋታታቸው ምክንያት ቤተሰባቸው ይፈርሳል። ውጥረት ያለባቸው ልጆች ቅዠት ሊያስቸግራቸው፣ ትምህርት የመቀበል ችግር ሊኖርባቸው፣ የመንፈስ ጭንቀት ሊይዛቸው ወይም ከሰዎች ጋር መቀላቀል ሊከብዳቸው ይችላል። እንዲያውም አንዳንዶቹ ስሜታቸውን መቆጣጠር ይቸግራቸዋል። ውጥረት ያለበት ልጅ አፋጣኝ እርዳታ ያስፈልገዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ