የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g24 ቁጥር 1 ገጽ 4-6
  • ለሌሎች አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለሌሎች አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?
  • ንቁ!—2024
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለሌሎች አክብሮት ማሳየት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ምን ጥረት እያደረግን ነው?
  • ለሌሎች አክብሮት አሳዩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?
    ንቁ!—2024
  • መቻቻል—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ለሥልጣን አክብሮት ማሳየት ያለብን ለምንድን ነው?
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2024
g24 ቁጥር 1 ገጽ 4-6
ምግብ ቤት ውስጥ ያለ አንድ ሰው አስተናጋጁን ሲሰድበው፤ አስተናጋጁ ይቅርታ እየጠየቀው ነው። ከሰውየው ጋር የተቀመጡት ሰዎች ተሳቀዋል።

ለሌሎች አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?

ለሌሎች አክብሮት ማሳየት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ለሌሎች አክብሮት ማሳየት ውጥረት የነገሠባቸውን ሁኔታዎች ለማርገብ ያስችላል፤ እንዲሁም አለመግባባቶች እንዳይባባሱ ያደርጋል።

  • አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ “የለዘበ መልስ ቁጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቁጣን ያነሳሳል” ይላል። (ምሳሌ 15:1) አክብሮት የጎደለው አነጋገርና ድርጊት እሳት ላይ ጭድ እንደመጨመር ነው፤ የከፋ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል።

  • ኢየሱስ “አንደበት የሚናገረው በልብ ውስጥ የሞላውን ነው” ብሏል። (ማቴ. 12:34) አክብሮት የጎደለው አነጋገር በልባችን ውስጥ ሥር የሰደደ ችግር እንዳለ ይኸውም ከእኛ የተለየ ዘር፣ ጎሳ፣ ብሔር ወይም የኑሮ ደረጃ ላላቸው ሰዎች መጥፎ አመለካከት እንዳለን ሊጠቁም ይችላል።

    በቅርቡ ከ28 አገሮች በተውጣጡ ከ32,000 የሚበልጡ ሰዎች ላይ አንድ ጥናት ተደርጎ ነበር። በጥናቱ ላይ ከተሳተፉት ሰዎች መካከል 65 በመቶ የሚሆኑት የአሁኑን ያህል መከባበር የጠፋበት ዘመን አይተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

በትምህርት ቤትም ሆነ በሥራ ቦታ ለሁሉም ሰዎች አክብሮት አሳይ፤ አመለካከታቸውን ባትጋራም እንኳ ልታከብራቸው ይገባል። ሊያግባቧችሁ የሚችሉ ነጥቦችን ፈልግ። ይህም ነቃፊ ከመሆን ወይም በእነሱ ላይ ከመፍረድ እንድትቆጠብ ይረዳሃል።

“እንዳይፈረድባችሁ በሌሎች ላይ አትፍረዱ።”—ማቴዎስ 7:1

ሌሎች እንዲይዙህ በምትፈልግበት መንገድ ሰዎችን ያዝ። ሌሎችን በአሳቢነትና በፍትሕ የምትይዝ ከሆነ እነሱም ተመሳሳይ ነገር ሊያደርጉልህ ይችላሉ።

“ልክ ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ እንደምትፈልጉት ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው።”—ሉቃስ 6:31

ይቅር ባይ ሁን። ሌሎች አክብሮት የጎደለው ነገር ሲናገሩ ወይም ሲያደርጉ ሆን ብለው እንዳደረጉት ከማሰብ ይልቅ በቸልታ ለማለፍ ሞክር።

“ጥልቅ ማስተዋል ሰውን ቶሎ እንዳይቆጣ ያደርገዋል፤ በደልንም መተዉ ውበት ያጎናጽፈዋል።”—ምሳሌ 19:11

በይሖዋ ምሥክሮች የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ያለው ሁኔታ። የተለያየ ዕድሜና ባሕል ያላቸው ሰዎች ሰላም ሲባባሉና ሲጨዋወቱ።
በይሖዋ ምሥክሮች የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ያለው ሁኔታ። የተለያየ ዕድሜና ባሕል ያላቸው ሰዎች ሰላም ሲባባሉና ሲጨዋወቱ።

ምን ጥረት እያደረግን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች በመኖሪያ አካባቢያቸውም ሆነ በሥራ ቦታቸው መከባበር እንዲሰፍን ጥረት ያደርጋሉ።

ለሁሉም ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እናስተምራለን። ሆኖም እምነታችንንም ሆነ አመለካከታችንን እንዲቀበሉ አናስገድድም። ከዚህ ይልቅ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር በመከተል መልእክታችንን “በገርነት መንፈስና በጥልቅ አክብሮት” ለማቅረብ ጥረት እናደርጋለን።—1 ጴጥሮስ 3:15፤ 2 ጢሞቴዎስ 2:24

ለአድልዎ ቦታ የለንም። አስተዳደጋቸውና ባሕላቸው ምንም ይሁን ምን መጽሐፍ ቅዱስን መማር ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ የጉባኤ ስብሰባዎቻችን ክፍት ናቸው። መቻቻል እንዲሰፍን ጥረት እናደርጋለን፤ እንዲሁም ‘ሁሉንም ዓይነት ሰው እናከብራለን።’—1 ጴጥሮስ 2:17

የመንግሥትን ሥልጣን እናከብራለን። (ሮም 13:1) ሕጉን እንታዘዛለን፤ እንዲሁም ግብር እንከፍላለን። በፖለቲካዊ ጉዳዮች ገለልተኛ ብንሆንም ሌሎች ሰዎች በፖለቲካዊ ጉዳዮች ረገድ የራሳቸውን ውሳኔ የማድረግ መብት እንዳላቸው እንገነዘባለን፤ ይህን መብታቸውንም እናከብራለን።

ሥዕሎች፦ “ፍቅር ጥላቻን ድል ማድረግ ይችላል?” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰዱ ሥዕሎች። 1. አንድ አረብ። 2. አንድ አይሁዳዊ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

ከልጅነታችን ጀምሮ ሌሎችን እንድንጠላ ከተማርን እነሱን ማክበር ከባድ ይሆንብናል። በሁለት ጠበኛ ብሔራት ውስጥ ያደጉ ሁለት ሰዎች ሌሎችን ማክበርን የተማሩት እንዴት እንደሆነ ተመልከት። ፍቅር ጥላቻን ድል ማድረግ ይችላል? የሚለውን ቪዲዮ jw.org ላይ ፈልግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ