የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • rs ገጽ 27-ገጽ 29
  • አዳምና ሔዋን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዳምና ሔዋን
  • ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-
  • አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወንድና ሴት ፈጠረ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት ይደመሰሳል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • አዳም ፍጹም ከነበረ እንዴት ኃጢአት ሊሠራ ቻለ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
rs ገጽ 27-ገጽ 29

አዳምና ሔዋን

ፍቺ:- አዳም የመጀመሪያው ሰብዓዊ ፍጡር ነበር። በተጨማሪም አድሃም የተባለው የዕብራይስጥ ቃል “ሰው”፣ “ምድራዊ ሰው” እና “የሰው ዘር” ተብሎ ይተረጐማል፤ ይህም ትክክል ነው። የመጀመሪያዋ ሴት ሔዋን የአዳም ሚስት ነበረች።

አዳምና ሔዋን ልብ ወለድ ሰዎች ነበሩን?

ሁላችንም የተገኘነው ከአንድ አባትና ከአንድ እናት እንደሆነ ማመን ምክንያታዊ አይደለምን?

“አብዛኞቹ ታላላቅ ሃይማኖቶች ሁሉም የሰው ዘሮች . . . ከመጀመሪያው አንድ ሰው የተገኙ ናቸው ብለው ሲሰብኩ የቆዩትን ትምህርት ዛሬ ሳይንስ አረጋግጦታል።”—ሄሪዲቲ ኢን ሂውማንስ (የሰው ልጆች ውርስ)፣ (ፊላደልፊያና ኒው ዮርክ፣ 1972)፣ አምራም ሻይንፌልድ፣ ገጽ 238

“አዳምና ሔዋን የሁሉም የሰው ዘር አባትና እናት እንደሆኑ ከብዙ መቶ ዘመናት በፊት የተነገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ዛሬም እውነት መሆኑ በሳይንስ ተረጋግጧል። በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች በሙሉ አንድ ቤተሰብ ናቸው።”—ዘ ሬስስ ኦቭ ማንካይንድ (የሰው ዘሮች)፣ (ኒው ዮርክ፣ 1978)፣ ሩት ቤነዲክትና ጀኔ ወልትፊሽ፣ ገጽ 3

ሥራ 17:26:- “[አምላክ] በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ [ሰው] ፈጠረ።”

መጽሐፍ ቅዱስ አዳም ሁሉንም የጥንት ሰዎች የሚወክል የልብ ወለድ ታሪክ ገጸ ባሕርይ አድርጎ ያቀርበዋልን?

ይሁዳ 14:- “ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ . . . ትንቢት ተናገረ።” (ሄኖክ የሁሉም የጥንት የሰው ዘሮች ሰባተኛ ትውልድ አልነበረም።)

ሉቃስ 3:23–38:- “ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር፤ . . . የዳዊት ልጅ፣ . . . የአብርሃም ልጅ፣ . . . የአዳም ልጅ።” (ዳዊትና አብርሃም በታሪክ የታወቁ ሰዎች ናቸው። ታዲያ አዳም በትክክል ሰው ነበር ብሎ መደምደም ምክንያታዊ አይሆንምን?)

ዘፍ. 5:3 አዓት:- “አዳምም አንድ መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፣ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ። ስሙንም ሤት ብሎ ጠራው።” (ሤትን የወለዱት የጥንት ሰዎች በሙሉ አልነበሩም። ወይም የጥንት ሰዎች በሙሉ 130 ዓመት ሲሞላቸው ልጅ አልወለዱም።)

እባብ ሔዋንን እንዳነጋገራት መገለጹ ታሪኩ በሙሉ ልብ ወለድ ነው ያሰኛልን?

ዘፍ. 3:1–4:- “እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ [“ብልህ” አዓት] ነበረ። ሴቲቱንም:- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ሴቲቱም ለእባቡ አለችው:- . . . ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ እግዚአብሔር አለ:- እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም። እባብም ለሴቲቱ አላት:- ሞትን አትሞቱም።”

ዮሐ. 8:44:- “[ኢየሱስ እንዲህ አለ:- ዲያብሎስ] . . . ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” (ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።) (ስለዚህ በኤደን የተነገረው የመጀመሪያው ውሸት ምንጭ ዲያብሎስ ነበር። እባቡን የሚታይ አፈ ቀላጤው አድርጎ ተጠቅሞበታል። የዘፍጥረት ታሪክ ልብ ወለድና ፍጥረታትን በመጠቀም ትምህርት ለመስጠት የሚሞክር ታሪክ አይደለም። በተጨማሪ ራእይ 12:9⁠ን ተመልከት።)

ምሳሌ:- ድምፁ ከሌላ ሥፍራ እንደሚመጣ በማስመሰል የሚናገሩ ተዋናዮች አሉ። ይሖዋ የበለዓምን አህያ አፍ አውጥታ እንድትናገር እንዳደረጋት ከሚገልጸው የዘኁልቁ 22:26–31 ታሪክ ጋር አወዳድር።

“ፊተኛው ሰው አዳም” ልብ ወለድ ሰው ከነበረ “ኋለኛው አዳም” ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ሊባል ነው?

1 ቆሮ. 15:45, 47:- “እንዲሁ ደግሞ:- ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ። የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው።” (ስለዚህ አዳም በአምላክ ላይ ኃጢአት የሠራ በእርግጥ በሕይወት የኖረ ሰው አይደለም ብሎ መካድ የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት መካድ ማለት ነው። እንዲህ የመሰለው ክህደት ኢየሱስ ሕይወቱን ለሰው ልጆች እንዲሰጥ ያደረገውን ምክንያት ወደ አለመቀበል ያደርሳል። ይህን አለመቀበል ደግሞ የክርስትናን እምነት መካድ ማለት ነው።)

ኢየሱስ ራሱ የዘፍጥረትን ታሪክ እንዴት ተመለከተው?

ማቴ. 19:4, 5:- “[ኢየሱስ] እንዲህ አለ:- ፈጣሪ በመጀመሪያ [አዳምንና ሔዋንን] ወንድና ሴት አደረጋቸው፣ አለም:- ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፣ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፣ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል [በ⁠ዘፍጥረት 1:27፤ 2:24 ላይ] አላነበባችሁምን?” (ኢየሱስ የዘፍጥረት መጽሐፍ እውነተኛ ታሪክ እንደሆነ ያምን ከነበረ እኛስ ልናምንበት አይገባንምን?)

አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-

‘አዳም ኃጢአት እንዲሠራ የአምላክ ፈቃድና ዕቅድ ነበር’

እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ብዙ ሰዎች እንደዚያ ይላሉ። ይሁን እንጂ እርስዎ አንድ ነገር እንዳደርግ ቢነግሩኝና ባደርግ ስለሠራሁት ሥራ ይኮንኑኛል? . . . ታዲያ አዳም ኃጢአት የሠራው በአምላክ ፈቃድ ከነበረ ለምን እንደ ኃጢአተኛ ተቆጥሮ ከኤደን ተባረረ? (ዘፍ. 3:17–19, 23, 24)’

ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ጥሩ ጥያቄ ነው። ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ እግዚአብሔር ምን ዓይነት አምላክ መሆኑን የሚመለከት ነው። አንድ ሰው እኛ ራሳችን ባወጣነው ዕቅድ መሠረት ቢሠራ እርሱን መኮነን ትክክል ወይም ፍቅር ያለበት ይሆናል?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ይሖዋ የፍቅር አምላክ ነው። (1 ዮሐ. 4:8) መንገዶቹ ሁሉ ፍትሐዊ ናቸው። (መዝ. 37:28፤ ዘዳ. 32:4 አዓት ) አዳም ኃጢአት እንዲሠራ የአምላክ ፈቃድ አልነበረም። እንዲያውም አምላክ አስጠንቅቆት ነበር። (ዘፍ. 2:17)’ (2) ‘አምላክ ዛሬ ለእኛ ምርጫ እንደሚሰጠን ሁሉ ለአዳምም የፈለገውን እንዲመርጥ ነፃነት ሰጥቶት ነበር። ፍጹም መሆኑ አለመታዘዝን እንዳይመርጥ አያግደውም ነበር። አዳም የአለመታዘዝ ውጤት ሞት እንደሚሆን ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም እንኳ በአምላክ ላይ ማመፅን መረጠ።’ (በተጨማሪ ገጽ 142, 143⁠ን ተመልከት።)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ