የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lff ትምህርት 36
  • በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን
  • ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠለቅ ያለ ጥናት
  • ማጠቃለያ
  • ምርምር አድርግ
  • በሁሉም ነገር ሐቀኞች ሁኑ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • ሐቀኛ መሆን ይክሳል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ሐቀኛ መሆን ምን ጥቅም ያስገኛል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
ለተጨማሪ መረጃ
ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
lff ትምህርት 36
ምዕራፍ 36. አንድ ሰው ሰነድ ላይ ሲፈርም

ምዕራፍ 36

በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

ሁላችንም ጓደኞቻችን ሐቀኛ እንዲሆኑ እንፈልጋለን። ይሖዋም ወዳጆቹ ሐቀኛ እንዲሆኑ ይፈልጋል። ሆኖም ሐቀኛ ያልሆኑ ሰዎች በሞሉበት ዓለም ውስጥ ይህን ባሕርይ ማሳየት ቀላል አይደለም። በሁሉም ነገር ሐቀኛ መሆን ምን ጥቅሞች አሉት?

1. ሐቀኛ እንድንሆን የሚያነሳሳን ዋነኛው ምክንያት ምንድን ነው?

ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ሐቀኛ መሆናችን ለይሖዋ ያለንን ፍቅርና አክብሮት ያሳያል። ይሖዋ የምናስበውንና የምናደርገውን ነገር ሁሉ እንደሚያውቅ አስታውስ። (ዕብራውያን 4:13) ሐቀኛ ለመሆን የምናደርገውን ጥረት የሚመለከት ከመሆኑም ሌላ ጥረታችንን ያደንቃል። ቃሉ እንዲህ ይላል፦ “ይሖዋ ተንኮለኛን ሰው ይጸየፋልና፤ ከቅኖች ጋር ግን የጠበቀ ወዳጅነት አለው።”—ምሳሌ 3:32

2. በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ሐቀኛ መሆናችንን የምናሳይባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ይሖዋ ‘እርስ በርሳችን እውነትን እንድንነጋገር’ ይፈልጋል። (ዘካርያስ 8:16, 17) ይህ ምን ነገሮችን ያካትታል? ለቤተሰባችን አባላት፣ ለሥራ ባልደረቦቻችን፣ ለክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም ለመንግሥት ባለሥልጣናት አንዋሽም ወይም የተዛባ መረጃ አንሰጥም። ሐቀኛ የሆኑ ሰዎች አይሰርቁም ወይም አያጭበረብሩም። (ምሳሌ 24:28⁠ን እና ኤፌሶን 4:28⁠ን አንብብ።) በተጨማሪም የሚጠበቅባቸውን ቀረጥ ይከፍላሉ። (ሮም 13:5-7) እነዚህንም ሆነ እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎች ነገሮችን በማድረግ “በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር” ጥረት እናደርጋለን።—ዕብራውያን 13:18

3. ሐቀኛ መሆን ምን ጥቅሞች አሉት?

ሐቀኛ በመሆን ረገድ ጥሩ ስም ስናተርፍ ሌሎች እምነት ይጥሉብናል። በጉባኤ ውስጥ ያሉ ሁሉ ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ እርስ በርስ እንዲተማመኑና የደህንነት ስሜት እንዲሰማቸው አስተዋጽኦ እናደርጋለን። ንጹሕ ሕሊና ይኖረናል። በተጨማሪም ሐቀኛ መሆናችን “አዳኛችን የሆነው አምላክ ትምህርት . . . ውበት እንዲጎናጸፍ” እንዲሁም ሌሎች ወደ እውነተኛው አምልኮ እንዲሳቡ ያደርጋል።—ቲቶ 2:10

ጠለቅ ያለ ጥናት

ሐቀኛ መሆንህ ከይሖዋ ጋር ያለህን ግንኙነት የሚነካው እንዴት እንደሆነ እንዲሁም በተለያዩ የሕይወትህ ክፍሎች ሐቀኛ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

4. ሐቀኝነት ይሖዋን ያስደስታል

መዝሙር 44:21⁠ን እና ሚልክያስ 3:16⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • እውነቱን መደበቅ እንደምንችል ማሰብ ሞኝነት የሆነው ለምንድን ነው?

  • ከባድ በሚሆንበት ጊዜም እንኳ እውነቱን ለመናገር ስንመርጥ ይሖዋ ምን የሚሰማው ይመስልሃል?

አንድ አባት በርከክ ብሎ ልጁ የምትነግረውን ሲሰማ። ከጠረጴዛው አጠገብ በብርጭቆ ያለ ጭማቂ ተደፍቷል

ልጆች እውነቱን ሲናገሩ ወላጆች ይደሰታሉ። እኛም እውነቱን ስንናገር ይሖዋ ይደሰታል

5. ምንጊዜም ሐቀኛ ሁን

ብዙ ሰዎች እውነቱን መናገር የማያዋጣበት ጊዜ እንዳለ ይሰማቸዋል። ሆኖም ሁልጊዜ ሐቀኛ መሆን ያለብን ለምንድን ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ።

ቪዲዮ፦ ለደስታ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ነገሮች—ንጹሕ ሕሊና (2:32)

‘ለደስታ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ነገሮች—ንጹሕ ሕሊና’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰዱ ትዕይንቶች። ቤን ለአለቃው ከባድ ጥፋት እንዳጠፋ ከነገረው በኋላ ሲጨባበጡ

ዕብራውያን 13:18⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ሁኔታዎች ሥር ሐቀኛ መሆን የምንችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩ፦

  • በቤተሰብ ውስጥ

  • በሥራ ወይም በትምህርት ቤት

  • በሌሎች ሁኔታዎች

6. ሐቀኛ መሆናችን ይጠቅመናል

ሐቀኛ መሆናችን አንዳንድ ችግሮች ሊያስከትልብን ይችል ይሆናል። ውሎ አድሮ ከሚያስገኘው ጥቅም አንጻር ግን ሐቀኝነት ሁሌም የተሻለ አማራጭ ነው። መዝሙር 34:12-16⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ሐቀኛ መሆንህ የተሻለ ሕይወት እንድትመራ የሚረዳህ እንዴት ነው?

ሀ. አንድ ባልና ሚስት ቡና እየጠጡ ሲጨዋወቱ ለ. ጋራዥ ውስጥ የሚሠራ አንድ ሜካኒክ አለቃው ሲያመሰግነው ሐ. መኪናው ውስጥ ያለ አንድ ሰው ለትራፊክ ፖሊስ መንጃ ፈቃዱን ሲያሳይ
  1. ሀ. ሐቀኛ ባልና ሚስት ጠንካራ ትዳር ይኖራቸዋል

  2. ለ. ሐቀኛ ሠራተኞች የአሠሪዎቻቸውን አመኔታ ያተርፋሉ

  3. ሐ. ሐቀኛ ዜጎች በመንግሥት ባለሥልጣናት ዘንድ ጥሩ ስም ይኖራቸዋል

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “አንዳንድ ትናንሽ ውሸቶችን መዋሸት ምንም ችግር የለውም።”

  • ይሖዋ ሁሉንም ዓይነት ውሸት ይጠላል ብለህ እንድታምን የሚያደርግህ ምንድን ነው?

ማጠቃለያ

ይሖዋ ወዳጆቹ፣ በሚናገሩትም ሆነ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ ሐቀኛ እንዲሆኑ ይፈልጋል።

ክለሳ

  • ሐቀኛ መሆናችንን የምናሳይባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

  • እውነቱን መደበቅ እችላለሁ ብሎ ማሰብ ሞኝነት የሆነው ለምንድን ነው?

  • ምንጊዜም ሐቀኛ መሆን የምትፈልገው ለምንድን ነው?

ግብ

ምርምር አድርግ

ወላጆች ልጆቻቸውን ሐቀኛ እንዲሆኑ ማስተማር የሚችሉት እንዴት ነው?

እውነቱን ተናገር (1:44)

የገባነውን ቃል መጠበቅ ምን ጥቅም አለው?

ቃላችሁን ጠብቁ፤ ትባረካላችሁ (9:09)

በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ላይውል ቢችልም እንኳ ቀረጥ መክፈል ያለብን ለምንድን ነው?

“ቀረጥ መክፈል ይኖርብሃል?” (መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1, 2011)

የማጭበርበር ድርጊት ይፈጽም የነበረ አንድ ሰው ሕይወቱን እንዲለውጥና በሐቀኝነት እንዲሠራ ያነሳሳው ምንድን ነው?

“ይሖዋ መሐሪና ይቅር ባይ እንደሆነ ተማርኩ” (መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1, 2015)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ