የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w08 2/1 ገጽ 3
  • መልስ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መልስ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለወላጆች ተጨማሪ እርዳታ
    ንቁ!—2019
  • እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ?
    እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ?
  • ምን ይመስልሃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2025
  • መልሶችህን ማሻሻል
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
w08 2/1 ገጽ 3

መልስ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት

“መተዳደሪያ ከማግኘት ጭንቀታችን መገላገል፣ ቤታችንን ከዚህ ቀደም አስበናቸው በማናውቃቸው እንደ አየር ማሞቂያና ማቀዝቀዣ ብሎም እንደ ምርጥ የሲዲ ማጫወቻ ባሉ ውድ የቅንጦት ዕቃዎች መሙላት እንዲሁም ከዓመት እስከ ዓመት ፍራፍሬ ከቤታችን እንዳይጠፋ ማድረግ ብንችልም እንኳ የመኖራችን ዓላማ ‘ምንድን ነው?’ ብለን መጠየቃችንን አናቆምም። ለመሆኑ ይህ ሁሉ ሩጫ ለምንድን ነው? ዓላማውስ ምንድን ነው?”​—ዴቪድ ማይርዝ፣ ሚሺገን፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው ሆፕ ኮሌጅ ውስጥ የስነ ልቦና ፕሮፌሰር

እኚህ ፕሮፌሰር ያነሱትን ጥያቄ ምን ብለህ ትመልሳለህ? ምናልባት አንዳንዶች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ጊዜ ማጥፋት ምን ያስፈልጋል ብለው ያስቡ ይሆናል። ይሁን እንጂ እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችን ችላ ብሎ ለማለፍ መሞከር ጫማህ ውስጥ ጠጠር ሲገባብህ ችላ ብለህ ጉዞህን ከመቀጠል ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ጫማህ ውስጥ ጠጠር መግባቱ መንገድህን እንዳትቀጥል አያግድህ ይሆናል፤ ነገር ግን ደስ እያለህ አትሄድም።

‘ሕይወት አሁን ካለው የተሻለ ዓላማ ይኖረው ይሆን’ ብለህ ጠይቀህ የምታውቅ ከሆነ እንዲህ ያለ ጥያቄ ያነሳኸው አንተ ብቻ አይደለህም። የሰዎችን ሥነ ምግባራዊ አቋም በሚመለከት እስከ ዛሬ ከተደረጉት ጥናቶች ሁሉ ተወዳዳሪ የሌለው ወርልድ ቫልዩ ሰርቬይ የተሰኘ አንድ ጥናት እንዳመለከተው በበርካታ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሰዎች ስለ “ሕይወት ትርጉምና ዓላማ” ያስባሉ።

እውነተኛ የአእምሮ ሰላም ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ከዚህ በታች ላሉት ሦስት ዐበይት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ያስፈልግሃል።

ወደ ሕልውና የመጣነው እንዴት ነው?

የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?

የወደፊቱ ጊዜ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?

ለእነዚህ ወሳኝ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው? ቀጣዮቹ ገጾች በመላምት ወይም በፍልስፍና ሳይሆን የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተውን መልስ ይዘዋል። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስህን ገልጠህ እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ