የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w09 2/1 ገጽ 8
  • አምላክ ስለ እኔ ያስባል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ስለ እኔ ያስባል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ያሉ ገዥዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • የዘላለም ሕይወት ጠላት
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
w09 2/1 ገጽ 8

አምላክ ስለ እኔ ያስባል?

የተለመዱት መልሶች፦

▪ “አምላክ ስለ እኔ ችግሮች የሚያስብበት ጊዜም የለው።”

▪ “ስለ እኔ ያስባል ብዬ አላምንም።”

ኢየሱስ ምን ብሏል?

▪ “አምስት ድንቢጦች አነስተኛ ዋጋ ባላቸው ሁለት ሳንቲሞች ይሸጡ የለም? ሆኖም አንዷም እንኳ በአምላክ ፊት አትረሳም። የእናንተ የራሳችሁ ፀጉር እንኳ በሙሉ የተቆጠረ ነው። ስለዚህ አትፍሩ፤ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ።” (ሉቃስ 12:6, 7) ከዚህ በግልጽ ማየት እንደሚቻለው አምላክ ስለ እኛ እንደሚያስብ ኢየሱስ አስተምሯል።

▪ “‘ምን እንበላለን?’ ወይም ‘ምን እንጠጣለን?’ ወይም ደግሞ ‘ምን እንለብሳለን?’ ብላችሁ ፈጽሞ አትጨነቁ። እነዚህ ነገሮች ሁሉ አሕዛብ አጥብቀው የሚፈልጓቸው ናቸው። በሰማይ የሚኖረው አባታችሁ እነዚህ ሁሉ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል።” (ማቴዎስ 6:31, 32) አምላክ በግለሰብ ደረጃ የሚያስፈልጉንን ነገሮች እንደሚያውቅ ኢየሱስ እርግጠኛ ነበር።

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ስለ እኛ እንደሚያስብ በማያሻማ ሁኔታ ይገልጻል። (መዝሙር 55:22፤ 1 ጴጥሮስ 5:7) የሚያስብልን ከሆነ ታዲያ በዛሬው ጊዜ ይህ ሁሉ መከራ የሚደርስብን ለምንድን ነው? አምላክ አፍቃሪና ሁሉን ቻይ ከሆነ መከራን ለማስወገድ አንድ ዓይነት እርምጃ የማይወስደውስ ለምንድን ነው?

የዚህ ጥያቄ መልስ ሰይጣን የዚህ ዓለም ገዥ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ሲሆን ይህንን እውነታ ብዙዎች አያውቁትም። ሰይጣን ኢየሱስን በፈተነው ጊዜ የዓለምን መንግሥታት በሙሉ ካሳየው በኋላ “ይህን ሁሉ ሥልጣንና የእነዚህን መንግሥታት ክብር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ይህ ሁሉ ለእኔ ስለተሰጠ እኔ ደግሞ ለፈለግሁት እሰጠዋለሁ” የሚል ግብዣ አቅርቦለታል።—ሉቃስ 4:5-7

ሰይጣንን የዚህ ዓለም ገዥ እንዲሆን ያደረገው ማን ነው? የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን አዳምና ሔዋን ጀርባቸውን ለአምላክ በመስጠት ሰይጣንን በታዘዙ ጊዜ ሰይጣን ገዥያቸው እንዲሆን የመረጡ ያህል ነበር። አዳምና ሔዋን ካመጹበት ጊዜ አንስቶ ይሖዋ አምላክ የሰይጣን አገዛዝ ከንቱ መሆኑ በጊዜ ሂደት እንዲታይ አድርጓል። ይሖዋ ሰዎች እንዲያገለግሉት አላስገደደም፤ ከዚህ ይልቅ ወደ እሱ መመለስ የምንችልበትን መንገድ ከፍቶልናል።—ሮም 5:10

አምላክ ስለ እኛ ስለሚያስብ ኢየሱስ ከሰይጣን አገዛዝ ነፃ እንዲያወጣን ዝግጅት አድርጓል። ኢየሱስ በቅርቡ “ሞት የማስከተል ኃይል ያለውን ዲያብሎስን በሞቱ አማካኝነት እንዳልነበረ [ያደርገዋል]።” (ዕብራውያን 2:14) በዚህ መንገድ ኢየሱስ ‘የዲያብሎስን ሥራ ያፈርሳል።’—1 ዮሐንስ 3:8

ምድር እንደገና ገነት ትሆናለች። በዚያ ጊዜ አምላክ “[የሰዎችን] እንባን ሁሉ ከዓይኖቻቸው ላይ ይጠርጋል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። ቀድሞ የነበሩት ነገሮች [ያልፋሉ]።”—ራእይ 21:4, 5a

[የግርጌ ማስታወሻ]

a አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምን እንደሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች ከተዘጋጀው ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ከተባለው መጽሐፍ ላይ ምዕራፍ 11⁠ን ተመልከት።

[በገጽ 8 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

ምድር እንደገና ገነት ትሆናለች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ