የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w09 11/1 ገጽ 3
  • አንድ ስህተት ወደ ሌላ ስህተት ይመራል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አንድ ስህተት ወደ ሌላ ስህተት ይመራል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ፈላስፋ፣ ክርስትናን ደግፎ የጻፈና ሰማዕት የነበረው ጀስቲን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • አፖሎጂስቶች—የክርስትና ጠበቆች ወይስ ፈላስፎች?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ክፍል 3—ክርስትናን ደግፈው የጻፉ ሰዎች (አፖሎጂስቶች) የሥላሴን መሠረተ ትምህርት አስተምረዋልን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • የተሳሳተ ትምህርት 2፦ ክፉዎች በእሳት ይቃጠላሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
w09 11/1 ገጽ 3

አንድ ስህተት ወደ ሌላ ስህተት ይመራል

ሐዋርያው ጳውሎስ በአንደኛው መቶ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ይኖሩ ለነበሩ ክርስቲያኖች እንዲህ የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቶ ነበር፦ “በክርስቶስ ላይ ሳይሆን በዓለም መሠረታዊ ነገሮች እንዲሁም በሰው ወግ ላይ በተመሠረተ ፍልስፍናና ከንቱ ማታለያ ማንም አጥምዶ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ።”—ቆላስይስ 2:8

ጳውሎስ እንዲህ ያለ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ከሁለተኛው መቶ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች ስለ እምነታቸው ማብራሪያ ለመስጠት የጥንት ፈላስፎችን ጽንሰ ሐሳቦች መጠቀም ጀመሩ። ይህን ያደረጉት ለምን ነበር? በሮም ግዛት ውስጥ በነበሩ የተማሩ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት የማግኘትና በዚህ መንገድ ብዙዎችን ወደ ክርስትና የመለወጥ ሐሳብ ስለነበራቸው ነው።

እንደዚህ ካደረጉት ክርስቲያኖች መካከል በጣም ታዋቂ የነበረው ጀስቲን ማርተር ሲሆን እሱም የአምላክ ቃል አቀባይ የሆነው ኢየሱስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር ከመምጣቱ ከረጅም ጊዜ በፊት ለግሪክ ፈላስፎች ራሱን እንደገለጠ ያምን ነበር። ጀስቲንና እንደ እሱ ዓይነት አስተሳሰብ የነበራቸው ሌሎች መምህራን፣ ፍልስፍና እና አፈ ታሪክ ከክርስትና ጋር መቀላቀሉ ይህ ሃይማኖት የሁሉንም የሰው ዘር ፍላጎት የሚያሟላ እንዲሆን ያደርገዋል የሚል አመለካከት ነበራቸው።

ጀስቲን ማርተር ያስፋፋው የክርስትና እምነት ብዙዎች ወደዚህ ሃይማኖት እንዲለወጡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። ይሁንና እነዚያ ክርስቲያኖች አንድን የተሳሳተ ትምህርት መቀበላቸው ሌሎች የተሳሳቱ ትምህርቶች እንዲወለዱ ምክንያት ሆኗል፤ እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ የክርስትና መሠረተ ትምህርት እንደሆኑ በስፋት የሚታመንባቸው ትምህርቶች እንዲፈጠሩ አድርጓል። ከዚህ ቀጥሎ በቀረቡት የማመሳከሪያ ጽሑፎች ላይ ያለውን ሐሳብ ከትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር ማወዳደርህ እነዚህ ትምህርቶች ምን ያህል የተሳሳቱ እንደሆኑ ለመገንዘብ ያስችልሃል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ