የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w11 3/1 ገጽ 23
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የጥንቱ ክርስትናና ፖለቲካዊ መንግሥት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • “ምግባረ መልካም ሴት”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • “ምግባረ መልካም ሴት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
w11 3/1 ገጽ 23

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጳውሎስ በኩል ክርስቲያናዊ ሰላምታ የላኩት “ከቄሳር ቤተሰብ የሆኑ” የተባሉት እነማን ናቸው?

▪ ሐዋርያው ጳውሎስ ከሮም ሆኖ ለፊልጵስዩስ ጉባኤ ደብዳቤ የጻፈው ከ60 እስከ 61 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን በመልእክቱ ውስጥ የጠቀሰው ቄሳር ንጉሠ ነገሥት ኔሮ ነበር። ይሁንና በፊልጵስዩስ ለሚገኙ ክርስቲያኖች ሰላምታ የላኩት የኔሮ ቤተሰብ የተባሉት እነማን ናቸው?—ፊልጵስዩስ 4:22

“ከቄሳር ቤተሰብ የሆኑት” የሚለው አባባል የሚያመለክተው የንጉሠ ነገሥቱን የቅርብ ዘመዶች ብቻ ነው ብሎ ማሰብ ስህተት ይሆናል። ከዚህ ይልቅ በሮምና በግዛቷ ውስጥ የሚገኙ ባሪያዎችንና ነፃ የወጡ ሰዎችን ጨምሮ ንጉሠ ነገሥቱን የሚያገለግሉ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ያካትታል። በመሆኑም ‘የቄሳር ቤተሰብ’ የሚለው አባባል በሺዎች የሚቆጠሩ አገልጋዮችን ይጨምራል። እነዚህ ሰዎች የንጉሠ ነገሥቱን ቤተ መንግሥቶች፣ ርስቶችና ንብረቶች ያስተዳድሩ ወይም ዝቅተኛ የሆኑ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር። እንዲያውም አንዳንዶቹ በመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ኃላፊነት ነበራቸው።

ከሁኔታው መረዳት እንደምንችለው በሮም ከሚኖሩት የንጉሠ ነገሥቱ አገልጋዮች መካከል አንዳንዶቹ ክርስቲያኖች ሆነው ነበር። እነዚህ ሰዎች ክርስቲያን የሆኑት ጳውሎስ ሰብኮላቸው ይሁን አይሁን የሚታወቅ ነገር የለም። ያም ሆነ ይህ በፊልጵስዩስ ጉባኤ ከሚገኙ ክርስቲያኖች ጋር ልዩ ቅርበት የነበራቸው ይመስላል። ፊልጵስዩስ ጡረታ የወጡ በርካታ ወታደሮችና የመንግሥት አገልጋዮች የሚኖሩባት የሮም ቅኝ ግዛት እንደመሆኗ መጠን በዚያ የሚገኙ አንዳንድ ክርስቲያኖች በጳውሎስ በኩል ሰላምታ ከላኩት ክርስቲያኖች ጋር ወዳጆች ሊሆኑ ይችላሉ።

በሙሴ ሕግ ውስጥ የተጠቀሰው የዋርሳነት ግዴታ ምንድን ነው?

▪ በጥንቷ እስራኤል አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይወልድ ከሞተ የትውልድ መስመሩ እንዲቀጥል ሲባል ወንድሙ የሟቹን ሚስት እንዲያገባ ይጠበቅበት ነበር። (ዘፍጥረት 38:8) ከጊዜ በኋላ ይህ ዝግጅት በሙሴ ሕግ ውስጥ የተካተተ ሲሆን የዋርሳነት ግዴታ በመባል ይታወቃል። በሩት መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውና ቦዔዝ ስላደረገው ነገር የሚተርከው ዘገባ ሟቹ ወንድሞች ከሌሉት ይህ ግዴታ ወደ ሌሎች ዘመዶቹ ሊተላለፍ እንደሚችል ያሳያል።—ሩት 1:3, 4፤ 2:19, 20፤ 4:1-6

በ⁠ማርቆስ 12:20-22 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ሰዱቃውያን የተናገሩት ሐሳብ የዋርሳነት ግዴታ በኢየሱስ ዘመን የተለመደ እንደነበር ይጠቁማል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን የኖረው ፍላቭየስ ጆሴፈስ የተባለው አይሁዳዊ ታሪክ ጸሐፊ ይህ ሕግ የቤተሰቡ የዘር ሐረግ እንዲጠበቅ ብቻ ሳይሆን የሟቹ ንብረት ከቤተሰቡ እጅ እንዳይወጣና ባሏን በሞት ያጣችው ሴት በቁሳዊ ነገሮች ረገድ ችግር እንዳያጋጥማት ለማድረግ እንደሚረዳ ተናግሯል። በዚያን ወቅት አንዲት ሚስት የባሏን ንብረት መውረስ አትችልም ነበር። ይሁንና ከዋርሳ የሚወለደው ልጅ የሞተውን ግለሰብ ንብረት የመውረስ መብት ነበረው።

የሟቹ ዘመድ የማይፈልግ ከሆነ የዋርሳነት ግዴታውን እንዲወጣ ሕጉ አያስገድደውም። ይሁንና አንድ ሰው ‘የወንድሙን ቤት ለመሥራት’ አለመፈለጉ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ይቆጠር ነበር።—ዘዳግም 25:7-10፤ ሩት 4:7, 8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ