የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 1/1 ገጽ 3
  • ለአንባቢያን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለአንባቢያን
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 1/1 ገጽ 3

ለአንባቢያን

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

እያነበብከው ያለው ይህ መጽሔት መታተም የጀመረው ሐምሌ 1879 ነው። ከዚያ ጊዜ ወዲህ ሁኔታዎች የተለዋወጡ ሲሆን በዚህ መጽሔት ላይም ብዙ ለውጦች ተደርገዋል። (ከላይ ያሉትን ፎቶዎች ተመልከት።) ከዚህ ወር እትም ጀምሮ ደግሞ በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ላይ ተጨማሪ ለውጦችን አድርገናል። እነዚህ ለውጦች ምንድን ናቸው?

በበርካታ አገሮች ውስጥ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሰዎች መረጃዎችን ለማግኘት ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ከመሆኑም በላይ ይህ ዘዴ የበለጠ ቀላል ሆኖላቸዋል። ጥቂት ቁልፎችን በመንካት በኢንተርኔት ላይ ብቻ የሚገኙ መረጃዎችን መመልከት ይቻላል። እንዲሁም በርካታ መጻሕፍትን፣ መጽሔቶችንና ጋዜጦችን ኢንተርኔት ላይም ማንበብ ይቻላል።

በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ያለውን ይህን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት www.jw.org የተባለውን ድረ ገጻችንን በአዲስ መልክ አዘጋጅተነዋል፤ በአዲስ መልክ የተዘጋጀው ድረ ገጻችን ይበልጥ ማራኪ ከመሆኑም ሌላ ለአጠቃቀም ምቹ ሆኗል። ይህን ድረ ገጽ የሚጎበኙ ሰዎች ከ430 በሚበልጡ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ጽሑፎችን ማንበብ ይችላሉ። ይሁንና ቀደም ሲል በመጽሔቶቻችን ላይ በቋሚነት ይወጡ የነበሩ አንዳንድ ዓምዶች ከዚህ ወር ጀምሮ የሚገኙት በድረ ገጻችን ላይ ብቻ ይሆናል።a

አንዳንዶቹን ርዕሶች በድረ ገጻችን ላይ ብቻ ማውጣት ስለምንጀምር ከዚህ ወር ጀምሮ ለሕዝብ የሚሰራጨው የመጠበቂያ ግንብ እትም 32 ገጽ ሳይሆን 16 ገጽ ይኖረዋል። በአሁኑ ወቅት መጠበቂያ ግንብ የሚታተመው በ204 ቋንቋዎች ነው። የመጽሔቱ ይዘት መቀነሱ መጽሔቱን በሌሎች ተጨማሪ ቋንቋዎች ለመተርጎም ያስችላል።

በመጽሔቱ ላይ የተደረጉት እነዚህ ማስተካከያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ሕይወት አድን መልእክት ለሰዎች ይበልጥ በስፋት ለማዳረስ እንደሚያስችለን ተስፋ እናደርጋለን። እንዲሁም ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት ያላቸውንና በውስጡ የሚገኘውን ትምህርት ለማወቅ የሚፈልጉ በርካታ አንባቢዎቻችንን የሚጠቅሙ፣ እውቀት የሚያስጨብጡና ትኩረት የሚስቡ ሐሳቦችን በሚታተሙት መጽሔቶችም ሆነ በድረ ገጻችን ላይ ማቅረባችንን እንቀጥላለን።

አዘጋጆቹ

a በድረ ገጻችን ላይ ብቻ ከሚወጡት ዓምዶች መካከል ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲመረምሩ የሚያበረታታው “ለታዳጊ ወጣቶች” የተባለው ዓምድና ወላጆች ሦስት ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆቻቸውን ለማስተማር እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀው “መጽሐፍ ቅዱስን መማሪያዬ” የተባለው ዓምድ ይገኙበታል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ