የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 7/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቤዛው—ከሁሉ የላቀ የአምላክ ስጦታ
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • ኢየሱስ ያድናል—እንዴት?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 7/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ለዘላለም መኖር ይቻላል?

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የሰው ልጆች ከሞት ነፃ እንዲወጡ የሚያስችለው ዝግጅት ምንድን ነው?

የመጀመሪያው ሰው አዳም ብዙ መቶ ዓመታት ኖሯል። ውሎ አድሮ ግን አርጅቶ መሞቱ አልቀረም። ከዚያ ጊዜ ወዲህ ሰዎች እርጅናን ለማስቀረት የተለያዩ ዘዴዎችን ሲሞክሩ ቆይተዋል። ሆኖም ከሞት ማምለጥ የቻለ ማንም የለም። ለምን? ምክንያቱም አዳም አርጅቶ የሞተው የአምላክን ትእዛዝ ጥሶ ኃጢአት በመሥራቱ ነው። እኛም ከአዳም ኃጢአትንና የኃጢአት ቅጣት የሆነውን ሞትን ስለወረስን እናረጃለን።—ዘፍጥረት 5:5⁠ን እና ሮም 5:12⁠ን አንብብ።

የሰው ዘሮች ለዘላለም መኖር እንዲችሉ ቤዛ የሚከፍልላቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል። (ኢዮብ 33:24, 25) ቤዛ ማለት አንድን ሰው ነፃ ለማውጣት የሚከፈል ካሳ ነው፤ እኛም ከሞት ነፃ መውጣት ያስፈልገናል። (ዘፀአት 21:29, 30) ኢየሱስ ስለ እኛ በመሞት ቤዛውን ከፍሎልናል።—ዮሐንስ 3:16⁠ን አንብብ።

የዘላለም ሕይወት ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

ከበሽታና ከእርጅና ነፃ የሚወጣው ሁሉም ሰው አይደለም። እንዲያውም እንደ አዳም አምላክን የማይታዘዙ ሰዎች የዘላለም ሕይወት ማግኘት አይችሉም። የዘላለም ሕይወት የሚያገኙት ኃጢአታቸው ይቅር የተባለላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው።—ኢሳይያስ 33:24⁠ን እና 35:3-6⁠ን አንብብ።

ይቅርታ ለማግኘት ደግሞ ልንወስደው የሚገባ እርምጃ አለ። የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት አምላክን ማወቅ ያስፈልገናል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ከሁሉ የተሻለ ሕይወት መምራት እንዲሁም የአምላክን ሞገስና የዘላለም ሕይወት ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስተምረናል።—ዮሐንስ 17:3⁠ን እና የሐዋርያት ሥራ 3:19⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ