የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 8/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እውነተኛውን ሃይማኖት ለይተህ ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • ሃይማኖቶች ወደፊት ምን ይጠብቃቸዋል?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • እውነተኛውን ሃይማኖት ለይተህ ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • አምላክ የሚቀበለው አምልኮ
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 8/1 ገጽ 16
የተለያየ ዘር ያላቸው የይሖዋ ምሥክሮች በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ አንድ ላይ ይሰበሰባሉ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ሁሉም ሃይማኖቶች አምላክን ያስከብራሉ?

በዓለም ላይ ስለሚፈጸሙ ነገሮች ዜና ስታዳምጥ አንዳንድ ጊዜ በሃይማኖት ስም ብዙ የክፋት ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ አስተውለህ ይሆናል። በእውነተኛው አምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ሁሉም ሃይማኖቶች አይደሉም። (ማቴዎስ 7:15) በእርግጥም በሐሰት ሃይማኖት የተነሳ አብዛኛው የሰው ልጅ ተሳስቷል።—1 ዮሐንስ 5:19⁠ን አንብብ።

ይሁን እንጂ አምላክ መልካምና እውነት የሆነውን ነገር ለሚወዱ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ትኩረት ይሰጣል። (ዮሐንስ 4:23) አምላክ እንደዚህ ላሉት ሰዎች ከቃሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን እንዲማሩ ግብዣ እያቀረበላቸው ነው።—1 ጢሞቴዎስ 2:3-5⁠ን አንብብ።

እውነተኛውን ሃይማኖት መለየት የምትችለው እንዴት ነው?

ይሖዋ አምላክ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ለመጡ ሰዎች እውነትን በማስተማርና እርስ በርስ እንዲዋደዱ በማሠልጠን አንድነት እንዲኖራቸው እያደረገ ነው። (ሚክያስ 4:2, 3) በመሆኑም እውነተኛውን ሃይማኖት የሚከተሉ ሰዎችን እርስ በርስ ባላቸው ፍቅር ለይተህ ልታውቃቸው ትችላለህ።—ዮሐንስ 13:35⁠ን አንብብ።

ይሖዋ አምላክ ሁሉም ዓይነት ሰዎች በእውነተኛው አምልኮ አማካኝነት አንድነት እንዲኖራቸው እያደረገ ነው።—መዝሙር 133:1

እውነተኛ የአምላክ ተከታዮች እምነታቸውና አኗኗራቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ያደርጋሉ። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) በተጨማሪም የአምላክን ስም ያከብራሉ። (ዘፀአት 6:3) እንዲሁም የሰው ልጅ ብቸኛ ተስፋ የአምላክ መንግሥት እንደሆነ ለሰዎች ይናገራሉ። (ዳንኤል 2:44) የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል ለሰዎች መልካም በማድረግ ‘ብርሃናቸው በሰው ፊት እንዲበራ’ ያደርጋሉ። (ማቴዎስ 5:16) በመሆኑም እውነተኛ ክርስቲያኖች፣ የአምላክን መንግሥት ምሥራች ለማካፈል ወደ ሰዎች ቤት በመሄድም ተለይተው ይታወቃሉ።—ማቴዎስ 24:14⁠ን፣ የሐዋርያት ሥራ 5:42⁠ን እና 20:20⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 15 ተመልከት

www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ