የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 1/1 ገጽ 13
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ክርስቶስ በመንግሥቱ በበጎችና በፍየሎች ላይ ይፈርዳል
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • የክርስቶስን ወንድሞች በታማኝነት መደገፍ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበረው ሕይወት​—እረኛው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 1/1 ገጽ 13
አንድን ጃንደረባ የሚያሳይ በድንጋይ ላይ የተቀረጸ የአሦራውያን ምስል

አንድን ጃንደረባ የሚያሳይ በድንጋይ ላይ የተቀረጸ የአሦራውያን ምስል

ይህን ያውቁ ኖሯል?

“ጃንደረባ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሠራበት እንዴት ነው?

ይህ ቃል፣ የተሰለበ ሰውን ለማመልከት የተሠራበት ጊዜ አለ። በጥንት ዘመን የነበረው አንዱ የቅጣት ዓይነት መስለብ ነበር፤ በተጨማሪም በምርኮ ወይም በባርነት የተወሰዱ አንዳንድ ወንዶች ይሰለቡ ነበር። እምነት የሚጣልባቸው የተሰለቡ ወንዶች፣ የንጉሣዊ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሴቶች የሚኖሩባቸውን ቤቶች ያስተዳድሩ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ሄጌና ሻአሽጋዝ የሚባሉት ጃንደረቦች የፋርሱን ንጉሥ (ቀዳማዊ ጠረክሲስ እንደሆነ ይታሰባል) ሚስቶችና ቁባቶች እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።—አስቴር 2:3, 14

ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ጃንደረባ ብሎ የሚጠራቸው ሁሉ የተሰለቡ ሰዎች ነበሩ ማለት አይደለም። አንዳንድ ምሁራን እንደሚናገሩት ቃሉ በቤተ መንግሥት ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ባለሥልጣን የሚያመለክት ሰፋ ያለ ትርጉም ነበረው። የኤርምያስ ተባባሪ የነበረውን አቤሜሌክንና ወንጌላዊው ፊልጶስ የሰበከለትን ስሙ ያልተጠቀሰ ኢትዮጵያዊ ለማመልከት ጃንደረባ የሚለው ቃል የገባው ከዚህ አንጻር ይመስላል። አቤሜሌክ፣ ንጉሥ ሴዴቅያስን በቀጥታ ያነጋግር እንደነበር ስለተገለጸ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን እንደነበረው ማየት ይቻላል። (ኤርምያስ 38:7, 8) “ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ” የነበረው ኢትዮጵያዊም የንግሥቲቱ ንብረት ኃላፊ እንደነበረ ተገልጿል።​—የሐዋርያት ሥራ 8:27

በጥንት ዘመን፣ እረኞች በጎችን ከፍየሎች የሚለዩት ለምን ነበር?

አንድ እረኛ ከመንጋው ጋር

ኢየሱስ ወደፊት የሚመጣውን የፍርድ ጊዜ አስመልክቶ ሲናገር ‘የሰው ልጅ በክብሩ ሲመጣ፣ እረኛ በጎቹን ከፍየሎቹ እንደሚለይ ሰዎችን አንዱን ከሌላው ይለያል’ ብሏል። (ማቴዎስ 25:31, 32) እረኞች፣ እነዚህን እንስሳት ይለያዩአቸው የነበረው ለምንድን ነው?

በአብዛኛው፣ ቀን ላይ በጎችና ፍየሎች አንድ ላይ ተሰማርተው እንዲግጡ ይደረጉ ነበር። ማታ ላይ ደግሞ በጎቹና ፍየሎቹ በዱር አራዊት፣ በሌቦችና በቅዝቃዜ እንዳይጠቁ ሲባል ጉረኖ ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል። (ዘፍጥረት 30:32, 33፤ 31:38-40) ይሁንና በጎቹና ፍየሎቹ የሚያድሩት በተለያዩ ጉረኖዎች ውስጥ ነበር፤ እረኞች ይህን የሚያደርጉት በተፈጥሯቸው ይበልጥ ጠበኛ የሆኑት ፍየሎች በአንፃራዊ ሁኔታ ሲታይ ገራም የሆኑትን በጎች፣ በተለይም እንስቶቹንና ግልገሎቻቸውን እንዳይጎዷቸው ለመጠበቅ ነበር። በተጨማሪም በጎቹ “በሚወልዱበት፣ በሚታለቡበትና በሚሸለቱበት” ጊዜ እረኛው ከፍየሎቹ ይለያቸው እንደነበር ኦል ቲንግስ ኢን ዘ ባይብል የተሰኘው መጽሐፍ ተናግሯል። በመሆኑም የኢየሱስ ምሳሌ በጥንቷ እስራኤል ውስጥ ከብት በማርባት በሚተዳደሩ አድማጮች ዘንድ በሚገባ የሚታወቅና በአእምሯቸው ውስጥ ምስል የሚፈጥር ነበር።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ