የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp22 ቁጥር 1 ገጽ 6-7
  • 1 | አታዳላ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 1 | አታዳላ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦
  • ምን ማለት ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ቲቶ “ስለ እናንተ አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • 3 | ጥላቻን ከአእምሮህ ነቅለህ አውጣ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
  • መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የሚቻለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
wp22 ቁጥር 1 ገጽ 6-7
አንድ ጥቁር ሰው የአንድን ነጭ ፎቶግራፍ ይዟል፤ አንድ ነጭ ሰው ደግሞ የአንድን ጥቁር ፎቶግራፍ ይዟል፤ በፎቶግራፉ ላይ ያሉት ሰዎች ፈገግ ብለዋል። ከጀርባ የተበሳጩ ሰዎች ፎቶግራፎች ይታያሉ።

የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የሚቻለው እንዴት ነው?

1 | አታዳላ

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦

“አምላክ እንደማያዳላ በእርግጥ አስተዋልኩ፤ ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና ትክክል የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።”—የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35

ምን ማለት ነው?

ይሖዋa አምላክ በዜግነታችን፣ በዘራችን፣ በቆዳ ቀለማችን ወይም በባሕላችን አይገምተንም። ከዚህ ይልቅ የሚያተኩረው በውስጣዊ ማንነታችን ላይ ነው። በእርግጥም “ሰው የሚያየው ውጫዊ ገጽታን ነው፤ ይሖዋ ግን የሚያየው ልብን ነው።”—1 ሳሙኤል 16:7

ምን ማድረግ ትችላለህ?

የሰዎችን ልብ ማንበብ ባንችልም አምላክን በመምሰል ሌሎችን ከአድልዎ ነፃ በሆነ መንገድ ለማየት ጥረት ማድረግ እንችላለን። ሰዎችን በቡድን ደረጃ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ለማየት ሞክር። ለሌሎች፣ ምናልባትም ሌላ ዘር ወይም ዜግነት ላላቸው ሰዎች አሉታዊ ስሜት እንዳለህ ካስተዋልክ ወደ አምላክ ጸልይ፤ እንዲህ ያለውን ስሜት ከልብህ ነቅለህ ለማውጣት እንዲረዳህ ጠይቀው። (መዝሙር 139:23, 24) አድልዎ ላለማድረግ እንዲረዳህ ይሖዋን ከልብህ ከጠየቅከው፣ ጸሎትህን ሰምቶ እንደሚረዳህ መተማመን ትችላለህ።—1 ጴጥሮስ 3:12

a ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው።—መዝሙር 83:18

“ከነጮች ጋር . . . በሰላም ጎን ለጎን ተቀምጬ አላውቅም። አሁን ግን የእውነተኛው የዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር አባል ሆኛለሁ።”—ታይተስ

እውነተኛ ታሪክ—ታይተስ

የጥላቻን ሰንሰለት በጥሷል

ታይተስ።

ታይተስ ጥቁሮችና ነጮች እንዳይቀላቀሉ የሚያዘው ጨቋኝ ሕግ ያበሳጨው ነበር፤ በመሆኑም የእሱን ዓይነት አቋም የሚያራምድ የወሮበሎች ቡድን አባል ሆነ። እንዲህ ብሏል፦ “በከተማ ውስጥ ጥቁሮች እንዲገቡባቸው ወዳልተፈቀዱ ሆቴሎችና ቡና ቤቶች ሄደን ብጥብጥ እናስነሳ ነበር።” ታይተስ ውስጡ በጥላቻ ተሞልቶ እንደነበር ሳይሸሽግ ተናግሯል። “ወንድም ሆነ ሴት ከማንም ሰው ጋር ብጋጭ ሁልጊዜም የመጀመሪያውን ቡጢ የምሰነዝረው እኔ ነበርኩ” ብሏል።

ታይተስ መጽሐፍ ቅዱስን ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ሲያጠና ለውጥ ማድረግ ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስን ማንበቡ በአመለካከቱ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። በተለይ ‘ሞት፣ ሐዘን፣ ጩኸትና ሥቃይ የማይኖርበት’ ዓለም እንደሚመጣ የሚገልጸው ተስፋ ልቡን ነካው።—ራእይ 21:3, 4

መጀመሪያ ላይ፣ ታይተስ በልቡ ውስጥ ያለውን ጥላቻ ማሸነፍ ከብዶት ነበር። “በአመለካከቴም ሆነ በአኗኗሬ ላይ ለውጥ ማድረግ አስቸጋሪ ሆኖብኝ ነበር” ብሏል። ሆኖም በሐዋርያት ሥራ 10:34, 35 ላይ ያገኘው ትምህርት በጣም ጠቅሞታል፤ ጥቅሱ አምላክ እንደማያዳላ ይናገራል።

ታዲያ ውጤቱ ምን ሆነ? ታይተስ እንዲህ ብሏል፦ “የይሖዋ ምሥክሮች የዘርና የቀለም ልዩነት ሳይበግራቸው እርስ በርስ እንደሚዋደዱ መመልከቴ እውነተኛውን ሃይማኖት እንደሚከተሉ እርግጠኛ እንድሆን አድርጎኛል። ተጠምቄ የይሖዋ ምሥክር ከመሆኔ በፊት እንኳ የጉባኤ አባል የሆነ አንድ ነጭ ሰው እቤቱ ምግብ ጋብዞኛል። ይህ ለእኔ እንደ ሕልም ነበር። ከነጮች ጋር እቤታቸው ቁጭ ብዬ ምግብ ልበላ ቀርቶ በሰላም ጎን ለጎን ተቀምጬ አላውቅም። አሁን ግን የእውነተኛው የዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር አባል ሆኛለሁ።”

የታይተስ ታሪክ በነሐሴ 1, 2009 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-29 ላይ ወጥቷል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ