የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w23 ታኅሣሥ ገጽ 32
  • ተሞክሮ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተሞክሮ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለሁሉም ሰው ርኅራኄ አሳዩ
  • እንደ ይሖዋ ሩኅሩኅ ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • ‘ከአንጀት የሚራራልን አምላካችን’
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
  • ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • “ርኅሩኆች” ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
w23 ታኅሣሥ ገጽ 32

ተሞክሮ

ለሁሉም ሰው ርኅራኄ አሳዩ

አንድ ቀን፣ በኒው ዚላንድ የምትኖር አንዲት እህት ‘አንዳችሁ ለሌላው አሳቢነት አሳዩ’ የሚለውን ቪዲዮ ተመለከተች፤ ቪዲዮው ይሖዋ ለሰዎች ከመራራት ባለፈ ርኅራኄውን በተግባር እንደሚያሳይ ይገልጻል። (ኢሳ. 63:7-9) እህታችን እሷም ለሌሎች ተግባራዊ እርዳታ በመስጠት የተማረችውን ነገር በሥራ ላይ ለማዋል ወሰነች። በዚያው ቀን አስቤዛ ለመግዛት ወጥታ ሳለ ጎዳና ላይ የምትኖር አንዲት ሴት አገኘች፤ ከዚያም ምግብ ልትገዛላት እንደምትችል ለሴትየዋ ነገረቻት። እሷም ግብዣዋን ተቀበለች። እህታችን ምግቡን ይዛ ስትመለስ መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል? የተባለውን ትራክት ተጠቅማ አጠር ያለ ምሥክርነት ሰጠቻት።

በዚህ ጊዜ ሴትየዋ ማልቀስ ጀመረች። በልጅነቷ የይሖዋ ምሥክር የነበረች ቢሆንም ከብዙ ዓመታት በፊት እውነትን እንደተወች ነገረቻት። ሆኖም ወደ እሱ ለመመለስ እንዲረዳት ወደ ይሖዋ መጸለይ ጀምራ ነበር። እህታችን ለሴትየዋ መጽሐፍ ቅዱስ የሰጠቻት ከመሆኑም ሌላ ጥናት እንድትጀምር ዝግጅት አደረገችላት።a

እኛም ዘመዶቻችንን እንዲሁም በጉባኤ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ጨምሮ ለሁሉም ሰው ርኅራኄ በማሳየት ይሖዋን መምሰል እንችላለን። በተጨማሪም ለሌሎች ለመመሥከር የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን በመፈለግ ርኅራኄ ማሳየት እንችላለን።

a የቀዘቀዙ ክርስቲያኖችን መርዳት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ በሰኔ 2020 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን “ወደ እኔ ተመለሱ” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ