የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 109
  • የዓለም መጨረሻ የሚመጣው መቼ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዓለም መጨረሻ የሚመጣው መቼ ነው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • የዓለም መጨረሻ አስፈሪ፣ ቀልብ የሚስብና ተስፋ የሚያስቆርጥ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የመጨረሻውን ዘመን በተመለከተ የሚነሱ አራት ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • “መጨረሻው” ምን ማለት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ይህ ዓለም ከጥፋት ይተርፍ ይሆን?
    ይህ ዓለም ከጥፋት ይተርፍ ይሆን?
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 109
የግድግዳ ሰዓት፤ 12 ሰዓት ሊል ነው

የዓለም መጨረሻ የሚመጣው መቼ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የዓለም መጨረሻ የሚመጣው መቼ እንደሆነ ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስ “ዓለም” የሚለውን ቃል የሚጠቀምበት እንዴት እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ ነው። አብዛኛውን ጊዜ “ዓለም” ተብሎ የሚተረጎመው ኮስሞስ የተባለው የግሪክኛ ቃል የሰው ልጆችን በተለይም ከአምላክና ከፈቃዱ ጋር ተስማምቶ የማይኖረውን የሰው ዘር ክፍል ለማመልከት ይሠራበታል። (ዮሐንስ 15:18, 19፤ 2 ጴጥሮስ 2:5) አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ኮስሞስ የሚለው ቃል ማኅበረሰቡ ያለበትን ሥርዓት ያመለክታል።—1 ቆሮንቶስ 7:31፤ 1 ዮሐንስ 2:15, 16a

“የዓለም መጨረሻ” ምንድን ነው?

“የዓለም መጨረሻ” የሚለው አገላለጽ በበርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን “የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። (ማቴዎስ 24:3) ይህ አገላለጽ የሚያመለክተው ምድር ወይም የሰው ልጆች በሙሉ እንደሚጠፉ ሳይሆን በምድር ላይ ያለው ሥርዓት እንደሚጠፋ ነው።—1 ዮሐንስ 2:17

መጽሐፍ ቅዱስ ‘ክፉ አድራጊዎች እንደሚጠፉና’ ጥሩ ሰዎች በምድር ላይ ተደስተው እንደሚኖሩ ይናገራል። (መዝሙር 37:9-11) ይህ ጥፋት የሚመጣው በአርማጌዶን ጦርነት በሚደመደመው ‘በታላቁ መከራ’ ወቅት ነው።—ማቴዎስ 24:21, 22፤ ራእይ 16:14, 16

የዓለም መጨረሻ የሚመጣው መቼ ነው?

ኢየሱስ “ስለዚያ ቀንና ሰዓት ከአብ ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ሆኑ ወልድ፣ ማንም አያውቅም” በማለት ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:36, 42) አክሎም ‘ባላሰባችሁት ሰዓት ይመጣል’ በማለት መጨረሻው የሚመጣው በድንገት እንደሆነ ጠቁሟል።—ማቴዎስ 24:44

መጨረሻው የሚመጣበትን ቀንና ሰዓት ማወቅ እንደማንችል የታወቀ ነው፤ ሆኖም ኢየሱስ የዓለም መጨረሻ መድረሱን እንድናውቅ የሚያስችሉንን ክንውኖች አጠቃሎ የያዘ “ምልክት” ሰጥቶናል። (ማቴዎስ 24:3, 7-14) መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ጊዜ ‘የፍጻሜው ዘመን፣’ እንዲሁም ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ በማለት ይጠራዋል።—ዳንኤል 12:4፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

ከዓለም መጨረሻ በኋላ የሚተርፍ ነገር ይኖራል?

አዎ። መጽሐፍ ቅዱስ “ምድር . . . ለዘላለም ከቦታዋ አትናወጥም” ስለሚል ምድር አትጠፋም። (መዝሙር 104:5) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ” ስለሚል በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ይኖራሉ። (መዝሙር 37:29) አምላክ ከመጀመሪያም የነበረውን ዓላማ ዳር ያደርሳል፦

  • ምድር ገነት ትሆናለች።—ኢሳይያስ 35:1፤ ሉቃስ 23:43

  • የሚያስፈራ ነገር የሌለበትና ሰላም የሰፈነበት ሕይወት ይኖራል።—ሚክያስ 4:4

  • ሁሉም ሰው ትርጉም ያለውና አርኪ ሥራ ይኖረዋል።—ኢሳይያስ 65:21-23

  • ሕመምና እርጅና አይኖርም።—ኢዮብ 33:25፤ ኢሳይያስ 33:24

በገነት ውስጥ ባሕር ዳርቻ ላይ የሚዝናኑ ሰዎች

a አዮን የሚለው የግሪክኛ ቃልም በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ “ዓለም” ተብሎ ተተርጉሟል። በዚህ መንገድ ሲተረጎም አዮን የሚለው ቃል ማኅበረሰቡ ያለበትን ሥርዓት ስለሚያመለክት ከኮስሞስ ጋር ተመሳሳይ ትርጉም ይኖረዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ