-
ዘፍጥረት 45:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ረሃቡ ገና ለአምስት ዓመታት ስለሚቀጥል እኔ የሚያስፈልግህን ምግብ እሰጥሃለሁ።+ አለዚያ አንተም ሆንክ ቤትህ እንዲሁም የአንተ የሆነው ሁሉ ችግር ላይ ትወድቃላችሁ።”’
-
-
ዘፍጥረት 47:13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 በዚህ ወቅት ረሃቡ እጅግ በርትቶ ስለነበር በመላው ምድር እህል አልነበረም፤ የግብፅም ምድር ሆነ የከነአን ምድር በረሃቡ የተነሳ በጣም ተጎድተው ነበር።+
-
-
ዘፍጥረት 47:19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 ዓይንህ እያየ ለምን እንለቅ? መሬታችንስ ለምን ጠፍ ሆኖ ይቅር? እኛንም ሆነ መሬታችንን በእህል ግዛን፤ እኛ ለፈርዖን ባሪያዎች እንሁን፤ መሬታችንም የእሱ ይሁን። በሕይወት እንድንኖርና እንዳንሞት እንዲሁም መሬታችን ጠፍ ሆኖ እንዳይቀር የምንዘራው እህል ስጠን።”
-