-
ዘፍጥረት 37:31-34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
31 ስለዚህ የዮሴፍን ቀሚስ ወሰዱ፤ አንድ ፍየል ካረዱ በኋላም ቀሚሱን ደሙ ውስጥ ነከሩት። 32 ከዚያም ያን ልዩ ቀሚስ እንዲህ ከሚል መልእክት ጋር ወደ አባታቸው ላኩት፦ “ይህን አገኘን፤ እባክህ ይህ የልጅህ ቀሚስ መሆን አለመሆኑን እስቲ እየው።”+ 33 እሱም ልብሱን አገላብጦ ካየው በኋላ “ይሄማ የልጄ ቀሚስ ነው! ኃይለኛ አውሬ በልቶት መሆን አለበት! በቃ ዮሴፍን አውሬ ቦጫጭቆታል ማለት ነው!” አለ። 34 ከዚያም ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ በወገቡም ላይ ማቅ ታጥቆ ለብዙ ቀናት ለልጁ አለቀሰ።
-