ዘፍጥረት 37:34, 35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ከዚያም ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ በወገቡም ላይ ማቅ ታጥቆ ለብዙ ቀናት ለልጁ አለቀሰ። 35 ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ሞከሩ፤ እሱ ግን ፈጽሞ ሊጽናና አልቻለም፤ “በልጄ ሐዘን እንደተቆራመድኩ ወደ መቃብር* እወርዳለሁ!”+ ይል ነበር። አባቱም ለልጁ ማልቀሱን አላቋረጠም። ዘፍጥረት 42:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 እሱ ግን እንዲህ አለ፦ “ልጄ ከእናንተ ጋር ወደዚያ አይወርድም። ምክንያቱም ወንድሙ ሞቷል፤ አሁን የቀረው እሱ ብቻ ነው።+ ከእናንተ ጋር አብሮ ሲሄድ መንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበትና ቢሞት ሽበቴን በሐዘን+ ወደ መቃብር*+ ታወርዱታላችሁ።” መዝሙር 88:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ነፍሴ* በመከራ ተሞልታለችና፤+ሕይወቴም በመቃብር* አፋፍ ላይ ነች።+
34 ከዚያም ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ በወገቡም ላይ ማቅ ታጥቆ ለብዙ ቀናት ለልጁ አለቀሰ። 35 ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ሞከሩ፤ እሱ ግን ፈጽሞ ሊጽናና አልቻለም፤ “በልጄ ሐዘን እንደተቆራመድኩ ወደ መቃብር* እወርዳለሁ!”+ ይል ነበር። አባቱም ለልጁ ማልቀሱን አላቋረጠም።
38 እሱ ግን እንዲህ አለ፦ “ልጄ ከእናንተ ጋር ወደዚያ አይወርድም። ምክንያቱም ወንድሙ ሞቷል፤ አሁን የቀረው እሱ ብቻ ነው።+ ከእናንተ ጋር አብሮ ሲሄድ መንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበትና ቢሞት ሽበቴን በሐዘን+ ወደ መቃብር*+ ታወርዱታላችሁ።”