ዘፍጥረት 15:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ይሁንና በባርነት በሚገዛቸው ብሔር ላይ እፈርዳለሁ፤+ እነሱም ብዙ ንብረት ይዘው ይወጣሉ።+ ዘፍጥረት 26:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በዚህ ምድር እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ ተቀመጥ፤+ እኔም ከአንተ ጋር መሆኔን እቀጥላለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ። ምክንያቱም ይህችን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤+ ደግሞም ለአባትህ ለአብርሃም እንዲህ ስል የማልሁለትን መሐላ እፈጽማለሁ፦+ ዘዳግም 31:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በፊትህ የሚሄደው ይሖዋ ነው፤ እሱ ምንጊዜም ከአንተ ጋር ይሆናል።+ አይጥልህም ወይም አይተውህም። አትፍራ ወይም አትሸበር።”+
3 በዚህ ምድር እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ ተቀመጥ፤+ እኔም ከአንተ ጋር መሆኔን እቀጥላለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ። ምክንያቱም ይህችን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤+ ደግሞም ለአባትህ ለአብርሃም እንዲህ ስል የማልሁለትን መሐላ እፈጽማለሁ፦+