ዘፍጥረት 25:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ከዚያም ወንድሙ ወጣ፤ በእጁም የኤሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤+ በዚህም የተነሳ ስሙን ያዕቆብ* አለው።+ ርብቃ እነሱን ስትወልድ ይስሐቅ 60 ዓመቱ ነበር። ዘፍጥረት 32:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ሰውየውም “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል* እንጂ ያዕቆብ አይባልም፤+ ምክንያቱም ከአምላክም ሆነ ከሰዎች ጋር ታግለህ+ በመጨረሻ አሸንፈሃል” አለው። ሆሴዕ 12:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በማህፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤+ባለ በሌለ ኃይሉም ከአምላክ ጋር ታገለ።+