ዘፍጥረት 17:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ከእንግዲህ ስምህ አብራም* አይባልም፤ የብዙ ብሔር አባት ስለማደርግህ ስምህ አብርሃም* ይሆናል። ዘፍጥረት 46:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ሴት ልጁን ዲናን+ ጨምሮ እነዚህ ሊያ በጳዳንአራም ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆች ናቸው። በአጠቃላይ ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹ 33 ነበሩ።* ዘፍጥረት 46:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የያዕቆብ ሚስት የራሔል ወንዶች ልጆች ዮሴፍና+ ቢንያም+ ነበሩ። 1 ዜና መዋዕል 2:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የእስራኤል+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ሮቤል፣+ ስምዖን፣+ ሌዊ፣+ ይሁዳ፣+ ይሳኮር፣+ ዛብሎን፣+ 2 ዳን፣+ ዮሴፍ፣+ ቢንያም፣+ ንፍታሌም፣+ ጋድ+ እና አሴር።+
2 የእስራኤል+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ሮቤል፣+ ስምዖን፣+ ሌዊ፣+ ይሁዳ፣+ ይሳኮር፣+ ዛብሎን፣+ 2 ዳን፣+ ዮሴፍ፣+ ቢንያም፣+ ንፍታሌም፣+ ጋድ+ እና አሴር።+