10 የአምላክ ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ በግልጽ ይታወቃሉ፦ በጽድቅ ጎዳና የማይመላለስ ሁሉ የአምላክ ወገን አይደለም፤ ወንድሙን የማይወድም የአምላክ ወገን አይደለም።+ 11 ከመጀመሪያ የሰማችሁት መልእክት እርስ በርሳችን መዋደድ አለብን የሚል ነውና፤+ 12 ከክፉው ወገን እንደሆነውና ወንድሙን በጭካኔ እንደገደለው እንደ ቃየን መሆን የለብንም።+ ቃየን ወንድሙን በጭካኔ የገደለው በምን ምክንያት ነበር? የእሱ ሥራ ክፉ፣+ የወንድሙ ሥራ ግን ጽድቅ ስለነበረ ነው።+