-
ዘፍጥረት 38:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን “ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ” አላት፤ ይህን ያላት ‘እሱም እንደ ወንድሞቹ ሊሞትብኝ ይችላል’ ብሎ ስላሰበ ነው።+ ስለዚህ ትዕማር ሄዳ በአባቷ ቤት መኖር ጀመረች።
-
-
ዘዳግም 25:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 “ወንድማማቾች አንድ ላይ ሲኖሩ ቆይተው ከመካከላቸው አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት የሟቹ ሚስት ከቤተሰቡ ውጭ የሆነ ሰው ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ወደ እሷ በመሄድ ሚስቱ አድርጎ ይውሰዳት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።+
-