-
ዘፀአት 26:22-25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 በስተ ምዕራብ በኩል ለሚገኘው ለኋለኛው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ስድስት ቋሚዎችን ትሠራለህ።+ 23 በማደሪያ ድንኳኑ በስተ ኋላ በኩል የማዕዘን ቋሚዎች እንዲሆኑ ሁለት ቋሚዎችን ትሠራለህ። 24 ቋሚዎቹም ከታች አንስቶ የመጀመሪያው ቀለበት እስከሚገኝበት እስከ ላይ ድረስ ድርብ መሆን አለባቸው። ሁለቱም በዚህ መንገድ መሠራት አለባቸው፤ እነሱም ሁለት የማዕዘን ቋሚዎች ሆነው ያገለግላሉ። 25 ስምንት ቋሚዎችና ከብር የተሠሩ 16 መሰኪያዎች ይኸውም በአንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች ይኖራሉ።
-