-
ዘፀአት 26:26-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
26 “ከግራር እንጨት አግዳሚ እንጨቶችን ታዘጋጃለህ፤ በአንዱ ጎን ላሉት የማደሪያ ድንኳኑ ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን፣+ 27 በሌላኛው ጎን ላሉት የማደሪያ ድንኳኑ ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን እንዲሁም በስተ ምዕራብ በኩል ባለው በኋለኛው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ላሉት ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን ታዘጋጃለህ። 28 በቋሚዎቹ መሃል ላይ የሚያርፈው መካከለኛው አግዳሚ እንጨት ከጫፍ እስከ ጫፍ የሚዘልቅ መሆን ይኖርበታል።
-