-
ዘፀአት 25:17-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 “እንዲሁም ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ትሠራለህ።+ 18 ሁለት የወርቅ ኪሩቦችን ትሠራለህ፤ ወርቁን በመጠፍጠፍም በመክደኛው ጫፍና ጫፍ ላይ ወጥ አድርገህ ትሠራቸዋለህ።+ 19 በሁለቱ የመክደኛው ጫፎች ላይ ኪሩቦቹን ሥራ፤ አንዱን ኪሩብ በዚህኛው ጫፍ፣ ሌላኛውን ኪሩብ ደግሞ በዚያኛው ጫፍ ላይ ሥራ። 20 ኪሩቦቹ ሁለቱን ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይከልሉታል፤+ እነሱም ትይዩ ይሆናሉ። የኪሩቦቹ ፊት ወደ መክደኛው ያጎነበሰ ይሆናል።
-