ዘፀአት 30:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “አሮንም+ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ያጨስበታል፤+ በየማለዳው መብራቶቹን+ በሚያዘገጃጅበት ጊዜም ዕጣኑ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል። ዘፀአት 40:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ከዚያም ለዕጣን የሚሆነውን የወርቅ መሠዊያ+ ከምሥክሩ ታቦት በፊት አስቀምጠው፤ ለማደሪያ ድንኳኑ መግቢያ የሚሆነውን መከለያም* በቦታው አድርገው።+ መዝሙር 141:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ጸሎቴ በአንተ ፊት እንደተዘጋጀ ዕጣን ይሁን፤+የተዘረጉት እጆቼ ምሽት ላይ እንደሚቀርብ የእህል መባ ይሁኑ።+ ራእይ 8:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የወርቅ ጥና* የያዘ ሌላ መልአክ መጥቶ በመሠዊያው+ አጠገብ ቆመ፤ እሱም የቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት እየተሰማ በነበረበት ወቅት በዙፋኑ ፊት ባለው በወርቁ መሠዊያ+ ላይ እንዲያቀርበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዕጣን+ ተሰጠው።
3 የወርቅ ጥና* የያዘ ሌላ መልአክ መጥቶ በመሠዊያው+ አጠገብ ቆመ፤ እሱም የቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት እየተሰማ በነበረበት ወቅት በዙፋኑ ፊት ባለው በወርቁ መሠዊያ+ ላይ እንዲያቀርበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዕጣን+ ተሰጠው።