-
ዘፀአት 30:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 “ዕጣን የሚጨስበት መሠዊያ ትሠራለህ፤+ ከግራር እንጨትም ትሠራዋለህ።+ 2 ርዝመቱ አንድ ክንድ፣* ወርዱ አንድ ክንድ ሆኖ አራቱም ጎኖቹ እኩል ይሁኑ፤ ቁመቱ ደግሞ ሁለት ክንድ ይሁን። ቀንዶቹም ከዚያው ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሆናሉ።+ 3 ላዩን፣ ሁሉንም ጎኖቹን እንዲሁም ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ ዙሪያውንም የወርቅ ክፈፍ ትሠራለታለህ። 4 በተጨማሪም በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ትሠራለታለህ፤ ቀለበቶቹም መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች የሚገቡባቸው ይሆናሉ። 5 መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው።
-