-
ዘፀአት 27:1-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 “ርዝመቱ አምስት ክንድ፣* ወርዱም አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ትሠራለህ።+ መሠዊያው አራቱም ጎኖቹ እኩል፣ ከፍታው ደግሞ ሦስት ክንድ መሆን አለበት።+ 2 በአራቱ ማዕዘኖቹ ላይ ቀንዶች+ ትሠራለታለህ፤ ቀንዶቹም የመሠዊያው ክፍል ይሆናሉ፤ መሠዊያውንም በመዳብ ትለብጠዋለህ።+ 3 አመዱን* ማስወገጃ ባልዲዎችን፣ አካፋዎችን፣ ሳህኖችን፣ ሹካዎችንና መኮስተሪያዎችን ትሠራለህ፤ ዕቃዎቹንም ሁሉ ከመዳብ ትሠራቸዋለህ።+ 4 ለመሠዊያው እንደ መረብ አድርገህ የመዳብ ፍርግርግ ትሠራለታለህ፤ በፍርግርጉ በአራቱም ማዕዘኖቹ ላይ አራት የመዳብ ቀለበቶችን ትሠራለታለህ። 5 ፍርግርጉንም ከመሠዊያው ጠርዝ ወደ ታች ወረድ አድርገህ ታስቀምጠዋለህ፤ ፍርግርጉም መሠዊያው መሃል አካባቢ ይሆናል። 6 ለመሠዊያው የሚሆኑ መሎጊያዎችን ከግራር እንጨት ትሠራለህ፤ በመዳብም ትለብጣቸዋለህ። 7 መሎጊያዎቹም ቀለበቶቹ ውስጥ ይገባሉ፤ መሠዊያውን በምትሸከሙበትም ጊዜ መሎጊያዎቹ በሁለቱ ጎኖቹ በኩል ይሆናሉ።+ 8 መሠዊያውንም ባዶ ሣጥን አስመስለህ ከሳንቃ ትሠራዋለህ። ልክ ተራራው ላይ ባሳየህ መሠረት ይሠራ።+
-
-
ዘፀአት 40:10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትም መሠዊያ እጅግ ቅዱስ እንዲሆን መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ ትቀባቸዋለህ፤ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ።+
-