-
ዘፀአት 10:16-19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 በመሆኑም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን በአስቸኳይ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በአምላካችሁ በይሖዋም ሆነ በእናንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁ። 17 ስለሆነም አሁን እባካችሁ ይህን ኃጢአቴን ብቻ ይቅር በሉኝ፤ ይህን ገዳይ መቅሰፍት ከእኔ ላይ እንዲያስወግድልኝም አምላካችሁን ይሖዋን ለምኑልኝ።” 18 እሱም* ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ ይሖዋንም ለመነ።+ 19 ከዚያም ይሖዋ ነፋሱ እንዲቀየር አደረገ፤ ነፋሱም ኃይለኛ የምዕራብ ነፋስ ሆነ፤ ነፋሱም አንበጦቹን ወስዶ ቀይ ባሕር ውስጥ ከተታቸው። በመላው የግብፅ ግዛት አንድም አንበጣ አልቀረም።
-