-
ዘፀአት 14:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 በኋላም ለግብፁ ንጉሥ ሕዝቡ እንደኮበለለ ተነገረው። ፈርዖንና አገልጋዮቹም ስለ ሕዝቡ የነበራቸውን ሐሳብ ወዲያው በመቀየር+ “ምን ማድረጋችን ነው? እስራኤላውያን ባሪያ ሆነው እንዳያገለግሉን የለቀቅናቸው ምን ነክቶን ነው?” አሉ።
-
-
ዘፀአት 14:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ግብፃውያኑ ተከታተሏቸው፤+ እስራኤላውያን በበዓልጸፎን ፊት ለፊት በባሕሩ አጠገብ ባለው በፊሃሂሮት ሰፍረው ሳሉም የፈርዖን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞቹና ሠራዊቱ በሙሉ ደረሱባቸው።
-