ዘፀአት 14:27, 28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ሙሴም ወዲያውኑ እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤ ሊነጋጋ ሲልም ባሕሩ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ተመለሰ። ግብፃውያንም ውኃው እንዳይደርስባቸው ለመሸሽ ሲሞክሩ ይሖዋ ግብፃውያኑን ባሕሩ መሃል ጣላቸው።+ 28 ውኃውም ተመልሶ እስራኤላውያንን ተከትለው የገቡትን የጦር ሠረገሎችና ፈረሰኞች እንዲሁም የፈርዖንን ሠራዊት በሙሉ አለበሳቸው።+ ከእነሱም መካከል አንድም የተረፈ የለም።+ መዝሙር 106:11, 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ውኃው ጠላቶቻቸውን ዋጠ፤ከእነሱ አንድ ሰው እንኳ አልዳነም።+ 12 በዚያን ጊዜ በገባው ቃል አመኑ፤+የውዳሴ መዝሙር ይዘምሩለት ጀመር።+
27 ሙሴም ወዲያውኑ እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤ ሊነጋጋ ሲልም ባሕሩ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ተመለሰ። ግብፃውያንም ውኃው እንዳይደርስባቸው ለመሸሽ ሲሞክሩ ይሖዋ ግብፃውያኑን ባሕሩ መሃል ጣላቸው።+ 28 ውኃውም ተመልሶ እስራኤላውያንን ተከትለው የገቡትን የጦር ሠረገሎችና ፈረሰኞች እንዲሁም የፈርዖንን ሠራዊት በሙሉ አለበሳቸው።+ ከእነሱም መካከል አንድም የተረፈ የለም።+