-
የሐዋርያት ሥራ 7:30-34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 “ከ40 ዓመትም በኋላ በሲና ተራራ አቅራቢያ በሚገኝ ምድረ በዳ፣ በሚነድ ቁጥቋጦ ነበልባል ውስጥ አንድ መልአክ ተገለጠለት።+ 31 ሙሴም ባየው ነገር ተደነቀ። ሆኖም ሁኔታውን ለማጣራት ወደዚያ ሲቀርብ የይሖዋ* ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማ፦ 32 ‘እኔ የአባቶችህ አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ።’+ በዚህ ጊዜ ሙሴ ይንቀጠቀጥ ጀመር፤ ሁኔታውን ይበልጥ ለማጣራትም አልደፈረም። 33 ይሖዋም* እንዲህ አለው፦ ‘የቆምክበት ስፍራ ቅዱስ መሬት ስለሆነ ጫማህን አውልቅ። 34 በግብፅ ባለው ሕዝቤ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና በእርግጥ አይቻለሁ፤ የጭንቅ ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤+ ልታደጋቸውም ወርጃለሁ። አሁንም ና፣ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ።’
-