-
ዘፀአት 31:13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እናንተን የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ መሆኔን እንድታውቁ የሚያደርግ፣ በትውልዶቻችሁ ሁሉ በእኔና በእናንተ መካከል ያለ ምልክት ስለሆነ በተለይ ሰንበቴን ማክበር አለባችሁ።+
-
-
ዘዳግም 5:15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ በብርቱ እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ እንዳወጣህ አስታውስ።+ አምላክህ ይሖዋ የሰንበትን ቀን እንድታከብር ያዘዘህ ለዚህ ነው።
-