-
ዕብራውያን 12:18-21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 እናንተ እኮ የቀረባችሁት ሊዳሰስ ወደሚችለውና+ በእሳት ወደተያያዘው ተራራ፣+ ወደ ጥቁሩ ደመና፣ ወደ ድቅድቁ ጨለማ፣ ወደ አውሎ ነፋሱ፣+ 19 ወደ መለከት ድምፁና+ ቃል ያሰማ ወደነበረው ድምፅ+ አይደለም፤ ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዳይነገራቸው ለምነው ነበር።+ 20 “እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት” የሚለው ትእዛዝ በጣም አስፈርቷቸው ነበርና።+ 21 በተጨማሪም በዚያ ይታይ የነበረው ነገር በጣም አስፈሪ ስለነበረ ሙሴ “ፈራሁ፤ ተንቀጠቀጥኩም” ሲል ተናግሯል።+
-