ዘፍጥረት 46:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አምላክም እንዲህ አለው፦ “እኔ የአባትህ አምላክ የሆንኩት እውነተኛው አምላክ ነኝ።+ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ ምክንያቱም በዚያ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።+ ዘዳግም 26:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘አባቴ ዘላን* አራማዊ+ ነበር፤ እሱም ወደ ግብፅ ወርዶ+ በቁጥር አነስተኛ ከሆነው ቤተሰቡ+ ጋር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ መኖር ጀመረ። ሆኖም በዚያ ሲኖር ኃያልና ቁጥሩ የበዛ ታላቅ ብሔር ሆነ።+ የሐዋርያት ሥራ 7:17-19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “አምላክ ለአብርሃም የተናገረው የተስፋ ቃል የሚፈጸምበት ጊዜ ሲቃረብ ሕዝባችን በግብፅ እየበዛና እየተበራከተ ሄደ፤ 18 ይህም የሆነው ዮሴፍን የማያውቅ ሌላ ንጉሥ በግብፅ እስከተነሳበት ጊዜ ድረስ ነው።+ 19 ይህ ንጉሥ በወገኖቻችን ላይ ተንኮል በመሸረብ ሕፃናት ልጆቻቸውን ለሞት አሳልፈው እንዲሰጡ አባቶቻችንን አስገደዳቸው።+
3 አምላክም እንዲህ አለው፦ “እኔ የአባትህ አምላክ የሆንኩት እውነተኛው አምላክ ነኝ።+ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ ምክንያቱም በዚያ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።+
5 አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘አባቴ ዘላን* አራማዊ+ ነበር፤ እሱም ወደ ግብፅ ወርዶ+ በቁጥር አነስተኛ ከሆነው ቤተሰቡ+ ጋር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ መኖር ጀመረ። ሆኖም በዚያ ሲኖር ኃያልና ቁጥሩ የበዛ ታላቅ ብሔር ሆነ።+
17 “አምላክ ለአብርሃም የተናገረው የተስፋ ቃል የሚፈጸምበት ጊዜ ሲቃረብ ሕዝባችን በግብፅ እየበዛና እየተበራከተ ሄደ፤ 18 ይህም የሆነው ዮሴፍን የማያውቅ ሌላ ንጉሥ በግብፅ እስከተነሳበት ጊዜ ድረስ ነው።+ 19 ይህ ንጉሥ በወገኖቻችን ላይ ተንኮል በመሸረብ ሕፃናት ልጆቻቸውን ለሞት አሳልፈው እንዲሰጡ አባቶቻችንን አስገደዳቸው።+