ዘፀአት 34:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ይሖዋ፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ* አምላክ በመሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ ለሌላ አምላክ አትስገድ።+ አዎ፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው።+ ማቴዎስ 4:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “አንተ ሰይጣን፣ ከፊቴ ራቅ! ‘ይሖዋ* አምላክህን ብቻ አምልክ፤+ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’+ ተብሎ ተጽፏልና” አለው። ሉቃስ 10:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው።
27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው።