ዘፍጥረት 9:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 አምላክ ሰውን በአምሳሉ ስለሠራው+ የሰውን ደም የሚያፈስ ማንም ሰው የእሱም ደም በሰው እጅ ይፈስሳል።+ ዘዳግም 5:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “‘አትግደል።+ ያዕቆብ 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “አታመንዝር”+ ያለው እሱ “አትግደል”+ የሚል ትእዛዝም ሰጥቷልና። እንግዲህ ምንዝር ባትፈጽምም እንኳ ከገደልክ ሕግ ተላላፊ ሆነሃል። 1 ዮሐንስ 3:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፤+ ነፍሰ ገዳይ የሆነ ሁሉ ደግሞ የዘላለም ሕይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ።+ ራእይ 21:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይሁን እንጂ የፈሪዎች፣ የእምነት የለሾች፣+ ርኩስና አስጸያፊ የሆኑ ሰዎች፣ የነፍሰ ገዳዮች፣+ የሴሰኞች፣*+ መናፍስታዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ የጣዖት አምላኪዎችና የውሸታሞች+ ሁሉ ዕጣ ፋንታቸው በእሳትና በድኝ በሚቃጠል ሐይቅ ውስጥ መጣል ነው።+ ይህ ሁለተኛውን ሞት ያመለክታል።”+
8 ይሁን እንጂ የፈሪዎች፣ የእምነት የለሾች፣+ ርኩስና አስጸያፊ የሆኑ ሰዎች፣ የነፍሰ ገዳዮች፣+ የሴሰኞች፣*+ መናፍስታዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ የጣዖት አምላኪዎችና የውሸታሞች+ ሁሉ ዕጣ ፋንታቸው በእሳትና በድኝ በሚቃጠል ሐይቅ ውስጥ መጣል ነው።+ ይህ ሁለተኛውን ሞት ያመለክታል።”+