ኢያሱ 24:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 “ስለዚህ ይሖዋን ፍሩ፤ በንጹሕ አቋምና* በታማኝነትም* አገልግሉት፤+ አባቶቻችሁ ከወንዙ* ማዶና በግብፅ ምድር ያገለገሏቸውን አማልክት አስወግዱ፤+ ይሖዋን አገልግሉ። ኢዮብ 28:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ሰውንም እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፣ ይሖዋን መፍራት ጥበብ ነው፤+ከክፉም መራቅ ማስተዋል ነው።’”+ ምሳሌ 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋን መፍራት* የእውቀት መጀመሪያ ነው።+ ጥበብንና ተግሣጽን የሚንቁት ሞኞች ብቻ ናቸው።+
14 “ስለዚህ ይሖዋን ፍሩ፤ በንጹሕ አቋምና* በታማኝነትም* አገልግሉት፤+ አባቶቻችሁ ከወንዙ* ማዶና በግብፅ ምድር ያገለገሏቸውን አማልክት አስወግዱ፤+ ይሖዋን አገልግሉ።