-
ዘሌዋውያን 6:2-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 “አንድ ሰው* በአደራ እንዲይዝ ወይም እንዲያስቀምጥ ከተሰጠው ነገር ጋር በተያያዘ+ ባልንጀራውን በማታለል ኃጢአት ቢሠራና በይሖዋ ላይ ታማኝነት የማጉደል ተግባር ቢፈጽም+ አሊያም ባልንጀራውን ቢሰርቅ ወይም ቢያጭበረብር 3 አሊያም ደግሞ የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ብሎ ቢዋሽና ሰውየው ከእነዚህ ኃጢአቶች መካከል አንዱንም እንዳልሠራ አድርጎ በሐሰት ቢምል+ እንዲህ ማድረግ አለበት፦ 4 ኃጢአት ቢሠራና በደለኛ ሆኖ ቢገኝ የሰረቀውን፣ ቀምቶ ወይም አጭበርብሮ የወሰደውን አሊያም በአደራ ተሰጥቶት የነበረውን ወይም ደግሞ ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፤ 5 አሊያም በሐሰት የማለበትን ማንኛውንም ነገር ይመልስ፤ ሙሉ ካሳ ይክፈል፤+ የዋጋውንም አንድ አምስተኛ ይጨምርበት። በደለኛ መሆኑ በተረጋገጠበትም ዕለት ለባለቤቱ ይሰጠዋል።
-