-
ዘፀአት 37:10-15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ከዚያም ከግራር እንጨት ጠረጴዛውን ሠራ።+ ርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ ከፍታው ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር።+ 11 በንጹሕ ወርቅም ለበጠው፤ ዙሪያውንም የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። 12 ከዚያም በዙሪያው አንድ ጋት* ስፋት ያለው ጠርዝ ሠራለት፤ ለጠርዙም ዙሪያውን የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። 13 በተጨማሪም አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠራለት፤ ቀለበቶቹንም አራቱ እግሮቹ በሚገኙባቸው አራት ማዕዘኖች ላይ አደረጋቸው። 14 ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች የሚይዙት ቀለበቶች በጠርዙ አጠገብ ነበሩ። 15 ከዚያም ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
-
-
ዘፀአት 40:22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 በመቀጠልም ጠረጴዛውን+ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በስተ ሰሜን በኩል ባለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ከመጋረጃው ውጭ አደረገው፤
-