የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 36:8-13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 ጥሩ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች+ ሁሉ በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍና ከደማቅ ቀይ ማግ ከተሠሩ አሥር የድንኳን ጨርቆች የማደሪያ ድንኳኑን ሠሩ፤+ እሱም* በጨርቆቹ ላይ ኪሩቦችን ጠለፈባቸው።+ 9 የእያንዳንዱ የድንኳን ጨርቅ ርዝመት 28 ክንድ* ወርዱ ደግሞ 4 ክንድ ነበር። ሁሉም የድንኳን ጨርቆች መጠናቸው እኩል ነበር። 10 ከዚያም አምስቱን የድንኳን ጨርቆች አንድ ላይ ቀጣጠላቸው፤ ሌሎቹን አምስት የድንኳን ጨርቆችም እንዲሁ አንድ ላይ ቀጣጠላቸው። 11 ከዚህ በኋላ አንደኛው የድንኳን ጨርቅ ከሌላኛው ጋር በሚጋጠምበት ጠርዝ ላይ ከሰማያዊ ክር ማቆላለፊያዎችን ሠራ። ሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ከዚህኛው ጋር በሚጋጠምበት በመጨረሻው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይም እንዲሁ አደረገ። 12 በአንደኛው የድንኳን ጨርቅ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ሠራ፤ ማቆላለፊያዎቹም ትይዩ እንዲሆኑ ሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ከዚህኛው ጋር በሚጋጠምበት የድንኳኑ ጨርቅ ጠርዝ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ሠራ። 13 በመጨረሻም 50 የወርቅ ማያያዣዎችን ሠርቶ የድንኳኑን ጨርቆች በማያያዣዎቹ አማካኝነት እርስ በርስ አጋጠማቸው፤ በዚህም መንገድ የማደሪያ ድንኳኑ አንድ ወጥ ሆነ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ