2 መቅረዙ፣+ ጠረጴዛውና በአምላክ ፊት የቀረበው ኅብስት+ የሚገኙበት የድንኳኑ የመጀመሪያው ክፍል ተሠርቶ ነበር፤ ይህም ቅድስት ይባላል።+ 3 ከሁለተኛው መጋረጃ+ በስተ ኋላ ግን ቅድስተ ቅዱሳን የሚባለው የድንኳኑ ክፍል ይገኝ ነበር።+ 4 በዚህ ክፍል ውስጥ የወርቅ ጥና+ እና ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተለበጠው+ የቃል ኪዳኑ ታቦት+ ይገኙ ነበር፤ በታቦቱ ውስጥም መና የያዘው የወርቅ ማሰሮ፣+ ያቆጠቆጠችው የአሮን በትርና+ የቃል ኪዳኑ ጽላቶች+ ነበሩ፤